News Detail
"በሀገራችን አሁን ላለው ችግር መነሻው የትምህርት ስርዓቱ ደካማ በመሆኑ ነው" ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ
የትምህርት ሚኒስትሩ ከኮተቤ ሜትሮፖሊታን ዩኒቨርሲቲ መምህራንና አስተዳደር ሰራተኞች ጋር ውይይት አካሂደዋል፡፡
ውይይቱም የኮተቤ ሜትሮፖሊታን ዩኒቨርሲቲ ወደ ኮተቤ ትምህርት ዩኒቨርሲቲ እንዲያድግ በመንግስት መወሰኑን ተከትሎ ዩኒቨርሲቲን መልሶ በጠንካራ መሰረት ላይ ማደራጀት በሚቻልበትና እና ሁሉም የድርሻውን እንዲወጣ ለማድርግ ያለመ ነው፡፡
አሁን በሀገሪቱ በተለያየ መንገድ የሚስተዋሉ ችግሮች ዋና መነሻው የትምህርት ስርዓቱ መውደቅ መሆኑን ሚኒስትሩ ገልፀዋል፡፡
በትምህርት ስርዓቱ ያለውን የትምህርት ጥራት መሰረታዊ ችግሮችን ከፖለቲካ አስተሳሰብ በማላቀቅና በጥልቀት በመረዳት ለመፍትሔው ሁሉም የድርሻውን መወጣት አለበትም ብለዋል፡፡
የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ብርሃነ መስቀል ጠና(ዶ/ር) ኮተቤ ትምህርት ዩኒቨርሲቲ ከጅምሩ ጀምሮ አሁን እስከ ደረሰበት ድረስ የነበሩ ስኬቶችና ከአደረጃጀት አንፃር የነበሩ ከፍተኛ ተግዳሮቶችን ለሚኒስትሩ አብራርተዋል፡፡
ዩኒቨርሲቲው በመምህራን ሙያ ልማት ቀዳሚ ዩኒቨርሲቲ እንደነበርም ገልፀው ዩኒቨርሲቲው በአዲስ መልክ የተቋቋመው በትምህርት ስርዓቱ ያሉ መሰረታዊ ችግሮችና ውድቀቶች ከስር መስረቱ በማጥናት ለመፍታት እንዲያስችል ነው ብለዋል፡፡
አሁን እንደ ሀገር በትምህርት ስርዓቱ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመፍታት ስርዓተ ትምህርቱን ማስተካከል፣ የትምህርት መሰረተ ልማቶችን በየትምህርት ተቋማቱ ሟሟላትና በየደረጃው ያሉ መምህራንን አቅም መገንባት ላይ በትኩረት እንደሚሰራ በመድረኩ ተገልጿል፡፡
ዩኒቨርሲቲው አሁን የተሰጠውን ተልዕኮ ሊመጥን የሚችል ራዕይና አደረጃጀት ቀርፆ ወደ ተግባር መግባት እንዳለበትም አቅጣጫ ተሰጥቷል፡፡
Recent News
በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የምግብ ሜኑ ተመሳሳይ እንዲሆን ተወሰነ።
Dec 09, 2024
የእንግሊዝኛ ቋንቋ ክህሎትን ለማሳደግ በትኩረት መስራት እንደሚገባ ተጠቆመ።
Dec 07, 2024