News Detail
በትምህርት ዘርፉ የኮቪድ-19 ክትባትን ተደራሽ ለማድረግ እየተሰራ ነው።
የኮቪድ-19 ስርጭትን በትምህርት ዘርፉ ውስጥ ለመቀነስ ክትባቱ ለመምህራን እና በትምህርት ዘርፉ ላይ ለሚሰሩ አካላት ለማዳረስ እየተሰራ መሆኑን የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።
በመድረኩም የኮቪድ -19 ክትባትን በትምህርት ዘርፉ በተለይ በትምህርት ቤት እና ዩኒቨርስቲዎች ተደራሽ ለማድረግ አስፈላጊው ዝግጅት መጠናቀቁም ተነግሯል።
የኮቪድ-19 ስርጭትን በትምህርት ቤት ለመቀነስ የመምህራን መከተብ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንደሚያደርግም ተገልጿል።
በዚህም መሰረት በቀጣይ ዘመቻ በመንግስት እና በግል ትምህርት ቤቶች የሚያስተምሩ መምህራንን የመከተብ ስራ እንደሚሰራ ነው የተገለፀው።
በተጨማሪም በኮቪድ-19 ክትባት ላይ ያለውን የተዛባ ግንዛቤም ለማሻሻል ትምህርት ቤቶች ላይ በቀጣይነት መሰራት እንዳለበትም ተጠቁሟል።
በመድረኩ የመምህራን ማህበርን ጨምሮ ከፌደራል እና ከክልል የተወጣጡ የጤና ቢሮ አመራሮች እንዲሁም በትምህርተ ዘርፉ ላይ የሚሰሩ አካላት ተሳትፈዋል።
ከዚህ ቀደም ትምህርት ሚኒስቴር በአዲስ አበባ ለሚገኙ 50ሺህ መምህራን ክትባት ለመስጠት ማቀዱ ይታወሳል።
Recent News
በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የምግብ ሜኑ ተመሳሳይ እንዲሆን ተወሰነ።
Dec 09, 2024
የእንግሊዝኛ ቋንቋ ክህሎትን ለማሳደግ በትኩረት መስራት እንደሚገባ ተጠቆመ።
Dec 07, 2024