News Detail
Nov 02, 2021
298 views
የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ከትርፍ ባለፈ ማህበረሰቡን ማገልገል እንዳለባቸው ተገለፀ።
ትምህርት ሚኒስቴር ከግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አመራሮች ጋር ምክክር አካሂዷል።
በምክክር መድረኩም የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ በትምህርት ዘርፉ ላይ ካሉ የግል ተቋማት ጋር ግልፅ መናበብ እንደሚያስፈልግ ገልፀዋል።
ሚኒስትሩ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በመንግስት ላይ የሚያነሱትን ቅሬታዎችን እንዲሁም ህብረተሰቡ በተቋማቱ ላይ የሚያነሳቸውን ቅሬታዎች እና ጥያቄዎች አንስተው ውይይት ተካሂዶባቸዋል።
ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ በቀጣይ የትምህርት ዘርፉ የሚሄድበትን አቅጣጫ እና ለውጦችም ለተሳታፊዎች ገልፀዋል።
በዚህም በመንግስት እና በግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እኩል ቁጥጥር እንደሚደረግ እና በመንግስት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሚሰጡ የመውጫ ፈተናዎች በግል ከፍተኛ ተቋማትም እንደሚሰጡ ተናግረዋል።
የግል ኮሌጆች የማስተማሪያ ፍቃድ አሰጣጥ ላይም ከፍተኛ ቁጥጥር እንደሚደረግም ገልፀዋል።
በመድረኩ የግል ከፍተኛ ተቋማት አመራሮችም ለተቋማቱ አፈፃፀም እንቅፋት ናቸው ያሏቸውን ሀሳቦች ለሚኒስትሩ አቅርበዋል።
ከዚህም ውስጥ የትምህርት አዋጁ ፣የመምህራን እጥረት፣ የመንግስት ድጋፍ አናሳ መሆን የተቋማቱ ተግዳሮቶች መሆናቸውን ነው የተናገሩት።
ከዚህ ቀደም ሚኒስቴሩ ከመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጋር ምክክር ማድረጉ ይታወሳል።
Recent News
በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የምግብ ሜኑ ተመሳሳይ እንዲሆን ተወሰነ።
Dec 09, 2024
የእንግሊዝኛ ቋንቋ ክህሎትን ለማሳደግ በትኩረት መስራት እንደሚገባ ተጠቆመ።
Dec 07, 2024