News Detail
Oct 06, 2021
1K views
የነጩ ፖስታ ለነጩ ቤተመንግስት ዘመቻ ፊርማችን በሽብርተኛው የህወሃት ቡድን ከትምህርት ገበታቸው ውጪ የሆኑ 3 ሚሊየን ተማሪዎችን የሚወክል ነው:- ጌታሁን መኩሪያ (ፒ ኤች ዲ) የትምህርት ሚኒስትር
የትምህርት ሚኒስቴር አመራሮች የኢትዮጵያን እውነታ ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ለማሳወቅ የተጀመረውን "ነጩ ፖስታ ለነጩ ቤተመንግስት" ዘመቻን ፊርማቸውን በማኖር አስጀምረዋል።
የትምህርት ሚኒስትሩ ጌታሁን መኩሪያ (ዶ/ር ኢንጂ.) የህወሃት የሽብር ቡድን ከ10ሺ በላይ ትምህርት ቤቶች ላይ ጉዳት በማድረስ ከ3ሚሊየን በላይ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታቸው ውጪ እንዲሆኑ አድርጓል ብለዋል።
በሽብር ቡድኑ ጥቃት ምክንያት በአማራ ክልል 1.5 ሚሊየን፣ በትግራይ ክልል ከ1.4 ሚሊየን፣ በአፋር ክልል ደግሞ 200ሺ በላይ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታቸው ውጪ ሆነዋል ያሉት ሚኒስትሩ ይህንን እውነት የአሜሪካው ፕሬዝዳንትና ካቢኔያቸው እንዲያውቁትና ቡድኑን ተጠያቂ እንዲያደርጉት እንፈልጋለን ብለዋል።
የህወሃት የሽብር ቡድን እስከ አሁን በትግራይ 6ሺ፣ በአማራ 3ሺ፣ በአፋር ደግሞ 500 ትምህርት ቤቶችን ከጥቅም ውጭ አድርጓቸዋል።
የትምህርት ሚኒስቴር የፈረመው ነጩ ፖስታ ለነጩ ቤተ መንግስት ዘመቻ ድምፃቸውን ማሰማት ላልቻሉ ከ3ሚሊየን በላይ ተማሪዎች ድምፅ የያዘ ነው።
Recent News
በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የምግብ ሜኑ ተመሳሳይ እንዲሆን ተወሰነ።
Dec 09, 2024
የእንግሊዝኛ ቋንቋ ክህሎትን ለማሳደግ በትኩረት መስራት እንደሚገባ ተጠቆመ።
Dec 07, 2024