News Detail
Oct 05, 2021
1K views
የትምህርት ሚኒስትሩ ጌታሁን መኩሪያ /ዶ/ር ኢንጅ./ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቀድሞ የተማሩበትን የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ጎበኙ፡፡
የትምህርት ሚኒስትሩ ጌታሁን መኩሪያ /ዶ/ር ኢንጅ./ እና የልዑካን ቡድናቸው ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ቀድሞ የተማሩበትን የበሻሻ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤትን ጎብኝተዋል፡፡
በጉብኝታቸው ወቅትም ለተማሪዎች የማነቃቂያ ንግግር ያደረጉ ሲሆን ልክ እንደ ክቡር ጠ/ሚ አብይ አህመድ ሀገር ተረካቢ ለመሆን ጠንክረው እንዲማሩና ትኩረታቸውን ትምህርታቸው ላይ ማድረግ እንዳለባቸው ተናግረዋል፡፡
ለአንድ ሀገር ግንባታ ትምህርት ወሳኝ መሆኑን ጠቅሰው ወላጆችም ልጆቻቸው ወደ ትምህርት ቤት በመላክና የልጆቻቸውን ትምህርት መከታተል እንዳለባቸውም አሳስበዋል፡፡
በመድረኩ የአካባቢው አባገዳዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎችና የትምህርት ቤቱ አስተዳደር ትምህርት ቤቱ አሁን ያለበትን ደረጃና ያጋጠሟቸውን ችግሮች ለክቡር ሚኒስትሩ አቅርበዋል፡፡
ትምህርት ቤቱን ለማደስና ምቹ የመማር ማስተማር ሂደትን ለመፍጠር የሚያስችል ድጋፍ እንደሚያደርጉም ሚኒስትሩ ቃል ገብተዋል፡፡
ክቡር ሚኒስትሩ ከዚህም በተጨማሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን የተከታተሉበት የበደሌ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤትንም አክለው ጎብኝተዋል፡፡
Recent News
በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የምግብ ሜኑ ተመሳሳይ እንዲሆን ተወሰነ።
Dec 09, 2024
የእንግሊዝኛ ቋንቋ ክህሎትን ለማሳደግ በትኩረት መስራት እንደሚገባ ተጠቆመ።
Dec 07, 2024