News Detail

National News
Jun 14, 2021 429 views

በ2014 ዓ.ም ከ50ሺህ በላይ ትምህርት ቤቶች ውስጥ የመንገድ ደህንነት ትምህርት ይሰጣል።

የመንገድ ደህንነት ስርዓተ ትምህርት ከቅደመ መደበኛ እስከ 12ኛ ክፍል እንዲሁም በጎልማሶች ትምህርት እንዲካተት ተደርጎ በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት የተቀረፀ ሲሆን በ2014 ወደ ስራ ይገባል።
የትምህርት ሚኒስትሩ ጌታሁን መኩሪያ (ዶ/ር ኢንጂ) በ 2014 ወደ ትግበራ የሚገባው አዲሱ ስርዓተ ትምህርት፣ የትምህርት ጥራትን ታሳቢ ያደረገና ባለፉት አመታት የታዩ ችግሮችን ነቅሶ ያወጣ መሆኑን ተናግረዋል።
በቀጣይ አመት ከ50ሺህ በላይ ትምህርት ቤቶች ውስጥ የመንገድ ደህንነት ትምህርት ተግባራዊ እንደሚደረግ የገለፁት ሚኒስትሩ የትራፊክ አደጋን ለመቀነስ የትራፊክ ደህንነት ትምህርት በስርዓተ ትምህርት ውስጥ መካተቱ በዜጎች ላይ የሚደርሰውን አደጋ እንዲቀንስ ያስችላል ብለዋል ።
የትራንስፖርት ሚነስትሯ ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ ደህንነቱ የተጠበቀ የመንገድ አጠቃቀምን ባህል ለማድረግና የትራፊክ አደጋን ለመቀነስ ሚኒስቴሩ ከተለያዩ ተቋማት ጋር በጋራ እየሰራ መሆኑን ገለፀዋል።
የመንገድ ደህንነት ትምህርት በስርዓተ ትምህርት ውስጥ መካተቱ ዘርፈ ብዙ ፋይዳ ከማምጣቱም በላይ የመንገድ አጠቃቀምን ባህል ለማድረግ የሚረዳ መሆኑን ሚኒስትሯ ገልፀዋል።
ስርዓተ ትምህርቱ ዜጎች የመንገድ ትራፊክ ህግና ደንብን በአግባቡ አውቀው ተግባራዊ እንዲያደርጉ እና ሌሎችንም እንዲያሳውቁ እድል እንደሚፈጥርም ተገልጿል።
በዝግጅቱም የመንገድ ደህንነት ትምህርትን ለማስተማር የሚያስችሉ ቋሳቁሶችን ትምህርት ሚኒስቴር ከትራንስፓርት ሚኒስቴር ተረክቧል።
በ2014 ተግባራዊ በሚደረገው የመንገድ ደህንነት ትምህርት ላይ
በ 11 የትምህርት አይነቶች የመንገድ ደህንነት ትምህርት የሚተገበር ሲሆን ከ 34 ሚሊየን በላይ ተማሪዎችን ለመድረስ ያስችላል።
Recent News
Follow Us