News Detail
Dec 31, 2020
608 views
የትምህርት ሴክተሩ ከሙስና የፀዳ እንዲሆን እየተሰራ ይገኛል፦ ትምህርት ሚኒስቴር
የትምህርት ሚኒስቴር በሀገር አቀፍ ደረጃ 16ኛ ጊዜ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ17ኛ ጊዜ እየተከበረ የሚገኘውን የፀረ ሙስና ቀንን ከፍተኛ አመራሮች እና ሰራተኞች በተገኙበት አክብሮ ውሏል።

በፕሮግራሙ ላይ የትምህርት ሚኒስትሩ ጌታሁን መኩሪያ (ፒ ኤች ዲ ) በትምህርት ሴክተሩ ላይ ሊኖሩ የሚችሉ የሙስና ስራዎችን በመከላከል እና በማስቀረት በስነ-ምግባር የታነፀ ትውልድ ለመፍጠር ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ይገኛል ብለዋል።
በትምህርት ስርዓቱም ግብረ ገብነት እንዲተገበር ትምህርት ሚኒስቴር እየሰራ መሆኑም በመድረኩ ተገልጿል።
ሙስና ከገንዘብ ጋር ብቻ የተገናኘ ሳይሆን ጊዜን በአግባቡ አለመጠቀም በራሱ ሙስና ነው ያሉት ሚነስትሩ ለጊዜ ዋጋ በመስጠት ሀገራችን የጣለችብንን ሃላፊነት ልንወጣ ይገባል ብለዋል ። በመድረኩም ላይ በፀረ ሙስና እንቅስቃሴዎች ዙሪያ ሰነድ ቀርቦ ተሳታፊዎች ውይይት አድርገውበታል።
ቀኑ "የትውልድ ስነ-ምግባር ግንባታን በጠንካራ ዲሲፒሊን በመምራት ሌብነትና ብልሹ አሰራር በመታገል የብልፅግና ጉዟችንን እናፋጥናለን" በሚል መሪ ቃል ነው ተከብሮ የዋለው።
የዘንድሮው የፀረ ሙስና ቀን በሀገራችን ለ16ኛ በ ዓለም አቀፍ ደረጃ ደግሞ ለ17ኛ ጊዜ እየተከበረ ይገኛል።