News Detail

የሀገር ውስጥ ዜና
Sep 08, 2020 780 views

የመማር ማስተማር ሂደቱን ለማስጀመር የሚያስችሉ ሁኔታዎችን እያጤንኩ ነው አለ ትምህርት ሚኒስቴር፡፡

የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ሚሊዮን ማቲዎስ የ2013 አ.ም.የትምህርት ሂደትን ለማስቀጠል የሚያስችሉ ከትምህርት ቤቶች አከፋፈት ጋር ተያይዞ ባሉ ወቅታዊ ሁኔታዎች ላይ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

የኮሮና ቫይረስ በኢትዮጵያ መከሰቱን ተከትሎ ከ42 ሺ በላይ ትምህርት ቤቶች ውስጥ ይማሩ የነበሩ ከ26 ሚሊየን በላይ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ውጭ ሆነዋል፡፡

የ2013 ዓመት ትምህርትን ለመጀመር የሚስችሉ ሁኔታዎችን ለመቃኘት የጥናት ቡደን ተቋቁሞ ጥናት እያደረገ መሆኑን ሚኒስትር ዴኤታው ተናግረዋል፡፡

በጥናቱ መሰረት ትምህርት ቤቶች በአንድ ክፍል ውስጥ ከ20 እስከ 25 ተማሪዎችን ለማስተማር የሚያስችል አቅም ስለመኖርና አለመኖራቸው ልየታ እየተካሄድ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡

የተማሪዎችን ርቀት ለማስጠበቅ በአንድ ወንበር አንድ ተማሪ እንዲቀመጥ የሚደረግ ሲሆን በፈረቃ ትምህርት መስጠት፣ ተጨማሪ የመማሪያ ክፍሎች መገንባት፣ የማህበረሰብ አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማትን ለማስተማሪያነት መጠቀም እንደ አማራጭ ጥቅም ላይ እንደሚውሉ ተገልጧል፡፡

ይህንን ታሳቢ በማድረግ አንዳንድ ክልሎች አስቀድመው ተጨማሪ የመማሪያ ክፍሎችን የገነቡ ቢሆንም ሁሉም ክልሎች በየትምህርት ቤቱ ተጨማሪ ክፍሎችን እንዲገነቡ እየተደረገ ነው።

በትምህርት ቤቶች ውስጥ ውሃ እንዲኖር ማድረግ፣ የእጅ ማፅጃ ሳኒታይዘርና ማስክ የማቅረብ ስራዎችም እንደሚሰሩ ተነስቷል፡፡

የኮረና ቫይረስ ስርጭት ያለበት ሁኔታ እየተገመገመ ደረጃ በደረጃ ትምህርት ቤቶችን ለመክፈት የሚያስችሉ ሁኔታዎች እየተጤኑ ነው ያሉት ሚስትር ዴኤታው ሚሊዮን ማቲዎስ ለስኬቱ ወላጆችና ባለድርሻ አካላት ከመንግስት ጎን እንዲቆሙ

Recent News
Follow Us