News Detail

የሀገር ውስጥ ዜና
Sep 02, 2020 1.4K views

የግል ትምህርት ቤቶች ምንም አይነት ተጨማሪ ክፍያ ማድረግ እንደማይችሉ የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የ 2013 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ምዝገባ ከ ነሃሴ 20 ጀምሮ እንዲከናወን ትምህርት ሚኒስቴር ማስታወቁን ተከትሎ ከተማሪዎች ምዝገባ እና ከትምህርት ክፍያ ጋር ተያይዞ ወላጆች ቅሬታን እያቀረቡ ይገኛሉ፡፡

ይህንንም ተከትሎ የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ሁሪያ አሊ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ተከትሎ የትምህርት ሚኒስቴር ያወጣውን የትምህርት ቤት ምዝገባ ክፍያ መመሪያን ተላልፈው ምዝገባ እያከናወኑ ያሉ ትምህርት ቤቶች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ እና ከመመሪያ ውጪ የሰበሰቡትን ገንዘብ ለወላጆች ተመላሽ እንዲያደርጉ አሳስበዋል፡፡

ሚኒስተር ዴኤታዋ አክለውም የ2013 የትምህርት ዘመን ምዝገባ ላይም ምንም አይነት የክፍያ ጭማሪ ማድረግ እንደማይቻል እና እንደሚያስጠይቅም ተናግረዋል፡፡

ትምህርት ቤቶችም ምዝገባ ሲያከናውኑ ከዚህ በፊት ይጠቀሙበት የነበረውን የክፍያ አቀባበል ዘዴ መቀየር የ ማይችሉ መሆኑን እና ከዚህ በፊት በነበረው የክፍያ ስርዓት መቀጠል እንዳለባቸውም ተገልጿል።፡

ከዚህም በተጨማሪ ትምህርት ቤቶች ከመደበኛ የትምህርት ክፍያ እና ከመመዝገቢያ ክፍያ ውጪ ሌሎች ተጨማሪ ክፍያ ማስከፈል ማይቻል መሆኑም ተነግሯል፡፡

የቀጣይ አመት ትምህርት የሚጀመርበትን ቀን በተመለከተም ሚኒስትር ዴኤታዋ ትምህርት ሚኒስቴር እስከሚያሳውቅ ድረስ ማንኛውም ትምህርት ቤት ትምህርት መጀመር እንደማይችል አስታውቀዋል፡፡

Recent News
Follow Us