News Detail

የሀገር ውስጥ ዜና
Aug 12, 2022 2.5K views

"የሚገነቡት ትምህርት ቤቶች ዘመናዊና የወደፊቷን ኢትዮጵያ የሚመስሉ ናቸው" ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ፤ የትምህርት ሚኒስትር

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በጦርነቱ ከወደሙ ትምህርት ቤቶች መካከል በሰሜን ወሎ ዞን በሐብሩ ወረዳ በመርሳ ከተማ መልካ ጨፌ ትምህርት ቤት ግንባታ መሠረት ድንጋይ ተቀመጧል፡

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ በአማራ እና አፋር ክልል ሙሉ በሙሉ የወደሙ 1ሺሕ 300 ትምህርት ቤቶችን በቀጣይ አምስት ዓመታት ውስጥ ለመገንባት መታቀዱን አንስተዋል።

የሚገነቡት ትምህርት ቤቶችም ዘመናዊና የወደፊቷን ኢትዮጵያ የሚመስሉ ናቸው ብለዋል።

የትምህርት ጥራትን ለማሻሻልና የተቋማቱን ደረጃ የማሳደግ ሥራ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ  በትኩረት እየሠራ መሆኑንም ሚኒስትሩ ገልጸዋል።

ፕሮፌሰር ብርሀኑ ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር በአማራ ክልል 8 ትምህርት ቤቶችን በአማራ እና አፋር ክልሎች የሚገነባውን  ሰዎች ለሰዎች  ግብረ ሰናይ ድርጅትም አመስግነዋል።

የሰሜን ወሎ ዞን አስተዳዳሪ ጋሻው አስማሜ  በበኩላቸው አሸባሪው ሕወሓት የሰሜን ወሎ ዞን የሚገኙ 777 ትምህርት ቤቶች ላይ ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ ውድመት ማድረሱን ገልጸዋል፡፡ 

በፕሮግራሙ ላይ የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ፋንታ ማንደፍሮ፣  የሰዎች ለሰዎች ድርጅት የኢትዮጵያ አገር አቀፍ ተጠሪ አቶ ይልማ ታዬን ጨምሮ  የሀብሩ ወረዳ  እና የመርሳ ከተማ አስተዳዳሪዎች  እንዲሁም መምህራን እና ተማሪዎች ተገኝተዋል።

Recent News
Follow Us