News Detail
May 12, 2022
3.2K views
ኢትዮጵያ በምርምርና ኢኖቬሽን ዘርፍ የአውሮፓ ህብረት የሆራይዘን ፈንድ ተጠቃሚ ለማድረግ እንደሚሰራ የአውሮፓ ህብረት አስታወቀ።
በአውሮፓ እና በኢትዮጵያ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መካከል ጠንካራ የምርምር ትብብር ለመጀመር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ በአዲስ አበባ ምክክር እየተደረገ ነው።
በመድረኩም የአውሮፓ ህብረት እና የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ላይ የተደረሰውን ስምምነት ተግባራዊ በሚደረግበት ዙሪያም ውይይት ተካሂዷል።
በአውሮፓ ህብረት የኢትዮጵያ አምባሳደር ሮናልድ ኮቢያ ረጅም ጊዜ የቆየውን የአውሮፓ ህብረት እና የኢትዮጵያ ግንኙነት በምርምርና በኢኖቬሽን ዘርፍ ለማሳደግ እንደሚሰሩ ተናግረዋል።
በትምህርት፣ በጤና፣ በሳይንስና ቴክኖሎጂ ዘርፍ የአውሮፓ ህብረትና ኢትዮጵያ በትብብር እየሰሩ መሆናቸውን ያነሱት አምባሳደሩ ኢትዮጵያ የአውሮፓ ህብረት ቀዳሚ ምርጫ መሆኗን ተናግረዋል።
በትምህርት ሚኒስቴር የሳይንስና ምርምር ጉዳዮች ዳይሬክተር ጀነራል ሰለሞን ቢኖር (ፒ ኤች ዲ) ተመራማሪዎች መንግስት የሚመድበውን በጀት ብቻ መጠበቅ ሳይሆን በዓለም አቀፍ ውድድሮች ውስጥ በመሳተፍ ከፍተኛ የምርምር ድጋፎችን ማሸነፍና ማምጣት እንደሚገባቸው ተናግረዋል።
ምክክሩ የአውሮፓ ህብረት የአፍሪካ ልዑካን ጽሕፈት ቤት በአፍሪካ በተለይም በኢትዮጵያ ስላለው እቅድ ለማስተዋወቅ፣ ከአውሮፓ ህብረት የሆራይዘን የምርምር አሸናፊዎችን ልምድ ለኢትዮጵያ ለማካፈልና እድሉን ማግኘት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ትኩረቱን ያደረገ ነው።