News Detail
Jan 13, 2022
1.2K views
በትምህርት ዘርፉ ላይ የመንግስትና የግል አጋርነት ዙሪያ ጥናት እየተካሄደ ነው።
የትምህርት ፋይናንስ እና የመንግስትና የግል አጋርነት በኢትዬጲያ የትምህርት ፓሊሲ ትግበራ ዙሪያ ጥናት እየተካሄደ ነው።
በጥናቱ ዙሪያ ከትምህርት ሚኒስቴር፣ ከግል ትምህርት ቤቶች፣ ከመንግስት መምህራን ማህበር እንዲሁም ከ አጋር ድርጅቶች ከተወጣጡ ባለሙያዎች ጋር ውይይት ተካሂዷል።
ጥናቱን የባህርዳር ዩኒቨርስቲ ከ ፕሪን ኢንተርናሽናል ኮሰልታንሲ ጋር በመሆን እንደሚሰሩት ተገልጿል።
ጥናቱ የትምህርት ዘርፉ ከ ግል ሴክተሩ ጋር በአጋርነት በመስራት ጥራትን ውጤታማነት ለማበረታታት ያለመ ነው።
ጥናቱ በሁሉም ክልሎች እና የከተማ አስተዳደሮች እንደሚደረግ እና ከ ቅድመ መደበኛ እስከ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ድረስ የሚያካትት እንደሆነም ተገልጿል።
በትምህርት ዘርፉ ውስጥ የሚስተዋለውን የፉይናንስ ችግር ለመፍታት የግል እና የመንግስት አጋርነት ያለበትን ደረጃ እና ምን መሆን እንዳለበት በጥናቱ እንደሚዳሰስ ተነግሯል ።
ጥናቱ የሁለቱ አጋርነት በትምህርት ተደራሽነት፣ፍትሀዊነት እና ጥራት ላይ የሚኖረውን አስተዋፆም የሚያመላክት ይሆናል ተብሏል።