News Detail

የሀገር ውስጥ ዜና
Jan 12, 2022 1.2K views

ኢትዬጵያን በመወከል በዲሞክራቲክ ኮንጎ ለሚካሄደው የፓን አፍረካ ስፓርታዊ ውድድር የሚሳተፉ ትምህርት ቤቶችን ለመመልመል የሚያስችል ስፓርታዊ ውድድር እየተካሄደ ነው።

በየካቲት ወር በዲሞክራቲክ ኮንጎ በሚካሄደው ከ16 አመት በታች የፓን አፍርካ የትምህርት ቤቶች የእግር ኳስ ስፖርት ውድድር ላይ ሀገራችንን ወክለው የሚሳተፉ ቡድኖች የሚመረጡበት አገር አቀፍ ውድድር በ አዲስ አበባ እየተካሄደ ነው።

በውድድሩም በሁለቱም ጾታዎች ኢትዮጵያን የሚወክሉ ቡድኖች ምርጫ እየተካሄደ ነው።

ውድድሩን  ትምህርት ሚኒስቴር ፣የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፍድሬሽን በጋራ አዘጋጅተውታል።

የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ  ፋንታ ማንደፍሮ ( ዶ/ር)   አህጉር አቀፍ ከ16 አመት በታች የትምህርት ቤቶች ስፖርት ውድድር አጠናክሮ ከመሄድ አንጻር ውድድሩ የስፖርት ልማቱን ለማጠናከር እንደሚያግዝ ገልፀዋል፡፡

 ዶ/ር ፋንታ አክለውም የዚህ አመት ተወዳዳሪዎች የላቀ ውጤት አስመዝግበው በፓን አፍሪካ የእግር ኳስ ስፖርት ውድድር መድረክ ኢትዮጵያን ከፍ እንደሚያደርጉ ያላቸውን ሙሉ እምነት ገልጸዋል፡፡

የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ሚኒስር ዴኤታ  አምባሳደር  መስፍን ቸርነት(ዶ/ር)  የውድድሩ ዓላማ ተማሪዎች በትምህርት ቤት ያገኙት የስፖርት ሳይንስ የንድፈ ሀሳብና የተግባር ትምህርት አቀናጅተው የመተግበር ብቃታቸው የሚፈተሽበት እና የወደፊት ተተኪ ስፖርተኞች በሀገር ደረጃ የሚፈሩበት ምቹ ሁኔታን ለመፍጠር እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

ትምህርት ሚኒስቴር የምስራቅ አፍሪካ የትምህርት ቤቶች ስፖርት ፌድሬሽን አባል መሆኑ ይታወቃል።

Recent News
Follow Us