News Detail
በአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን የወደሙ የትምህርት ተቋማትን መልሶ ለመገንባት ባለድርሻ አካላት ርብርብ እንዲያደርጉ የትምህርት ሚኒስቴር ጥሪ አቀረበ፡፡
በመድረኩም አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን በወረራቸው አካባቢዎች ካደረሰው ሰብዓዊ ጥፋት በተጨማሪ የትምህርት እና ሌሎች ሕዝብ የሚገለገልባቸውን ማኅበራዊ ተቋማት በማውደም የሕዝብ ጠልነቱን አሳይቷል ተብሏል፡፡
የአሸባሪ ቡድን በአማራ ክልል ብቻ በወረራቸው አካባቢዎች ከ4 ሺህ በላይ ትምህርት ቤቶች እንደወደሙ ተመላቷል፡፡
በዚህም ምክያት ከ1 ነጥብ 9 ሚሊየን በላይ ሕፃናትና ታዳጊዎች ከትምህርት ገበታ ውጭ ሆነዋልም ተብሏል፡፡
እነዚህን የወደሙ የትምህርት ተቋማት መልሶ ለመገንባት እና ትምህርት ለማስጀመር ከ11 ቢሊዬን ብር በላይ እንደሚያስፈልግም የክልሉ ትምህርት ቢሮ በጥናት አመልክቷል።
የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕሮፌሰር ) በአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን የወደሙ ትምህርት ቤቶች መልሰው ሲገነቡ በነበሩበት ደረጃ ሳይሆን በተሻለ ጥራት እንደሚሆን ተናግረዋል። በዚህም ሁሉም ባለድርሻ አካላት ርብርብ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።
በምክክሩ ላይ ከየፌዴራል እና የክልል የሥራ ኀላፊዎች እና የሚመለከታው አካላት ተገኘተዋል፡፡
Recent News
በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የምግብ ሜኑ ተመሳሳይ እንዲሆን ተወሰነ።
Dec 09, 2024
የእንግሊዝኛ ቋንቋ ክህሎትን ለማሳደግ በትኩረት መስራት እንደሚገባ ተጠቆመ።
Dec 07, 2024