News Detail
Dec 09, 2021
320 views
የብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀን ተከበረ፡፡
ወንድማማችነት ለህብረ-ብሄራዊ አንድነት! በሚል መሪ ቃል ለ16ኛ ጊዜ የሚከበረውን የኢትዮጵያ ብሄሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀን የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አመራሮችና ሠራተኞች በተገኙበት ተከብሯል፡፡
የዘንድሮው የብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን ሲከበር በተለያዩ ዘርፎች አንድነታችንን በማስጠበቅ ሀገራችንን ለማስቀጠል በየግንባሩ እየተዋደቁ ለሚገኙት ዜጎች ምስጋና እንደሚገባቸውም ተገልፀዋል፡፡
በመድረኩ የመወያያ ሰነድ በትምህርት ሚኒስቴር ባለሙያዎች ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡
ይህ በዓል ኢትዮጵያ ብዝሀነት ያለባት ሃገር መሆኗን እውቅና ከመስጠት ባለፈ ብሄሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦች በልዩነት ውስጥ ያለ አንድነታቸውን የሚያጠናክሩበት ነውም ተብሏል፡፡
ሠራተኞቹም በሰጡት አስተያየት የብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀንን ከማክበር ባለፈ ወቅቱ አንድነታችንን የምናጠናክርበትና በየተሰማራንበት ግንባር ውጤታማ የምንሆንበት ሊሆን ይገባል ብለዋል፡፡
በተጨማሪም የፀረ ሙስና ቀንም በስነ ምግባር የታነፀ አመራር ከሙስና ለፀዳች ኢትዮጵያ በሚል መሪቃል ሰነድ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡
Recent News
በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የምግብ ሜኑ ተመሳሳይ እንዲሆን ተወሰነ።
Dec 09, 2024
የእንግሊዝኛ ቋንቋ ክህሎትን ለማሳደግ በትኩረት መስራት እንደሚገባ ተጠቆመ።
Dec 07, 2024