News Detail

የሀገር ውስጥ ዜና
Nov 08, 2021 348 views

የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባና የትምህርት ሚነስትሩ የ12ኛ ክፍል ፈተና አስጣጥን በተለያዩ ትምህርት ቤቶች በመገኘት ተመለከቱ

የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሀኑ ነጋ ( ፕሮፌሰር) እና የአዲስ አበባ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በአዲስ አበባ በሚገኙ በተለያዩ ትምህርት ቤቶች በመገኘት የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና አሰጣጥን ተመልክተዋል።
በጉብኝቱም የመንግስት እና የግል ትምህርት ቤቶች የፈተና አሰጣጥ ሂደት ምን እንደሚመስል ምልከታ ተካሂዷል።
 
የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሀኑ ነጋ (ፕሮፌሰር) የዛሬውን ሀገር አቀፍ ፈተና ለመውሰድ ከተመዘገቡት ውስጥ 91.5% የሚሆኑ ተማሪዎች ፈተናውን እየወሰዱ መሆኑን ገልፀዋል።ፈተናውም በሁሉም አካባቢ በሰላም እየተሰጠ መሆኑንም ሚኒስትሩ ተናግረዋል።
 
የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በ አዲስ አበባ ፈተናው ሰላማዊ በሆነ ሁኔታ በ64 ጣቢያዎች እየተሰጠ መሆኑን ገልፀው በሁሉም ቦታ አስፈላጊው ጥበቃ እየተደረገ እና በተቀመጠው መስፈርት መሰረትም ፈተናው እየተሰጠ መሆኑን ተናግረዋል።
 
ሚኒስትሩ እና ከንቲባዋ ተማሪዎቹ ፈተናውን በተረጋጋ መንፈስ እንዲወስዱ መልዕክታቸውን አስተላልፈው ተማሪዎችን አበረታተዋል።
 
የ 2013 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና በዛሬው እለት በሁሉም አካባቢዎች እየተሰጠ ይገኛል። ፈተናው እስከ ህዳር 02/2014 እንደሚቆይ ይታወቃል።
Recent News
Follow Us