News Detail
Nov 01, 2021
311 views
ለ 1,500 ርዕሳነ መምህራን የአመራርነት ስልጠና ሊሰጥ ነው ።
በናሙናነት በተመረጡ አምስት መቶ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ውስጥ ለሚገኙ አንድ ሺህ አምስት መቶ ርዕሳነ- መምህራን የአመራርነት ብቃት ማሻሻያ ስልጠና ሊሰጥ መሆኑ ተገለፀ፡፡
ስልጠናውን ትምህርት ሚኒስቴር ከ ኢዲቲ ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር በመጪው ህዳር ወር የሚሰጥ ይሆናል።
የስልጠናው ዋነኛ ዓላማ ርዕሳነ-መምህራኑን በማብቃት የመማር ማስተማር ሂደቱን የበለጠ ለማጎልበት መሆኑን በኢዲቲ ኢትዮጵያ የታርጌት ፕሮጀክት ብሄራዊ የትምህርት አመራሮች ስልጠና መሪ ትዕግስት ተፈራ ገልጸዋል፡፡
በትምህርት ሚኒስቴር የመምህራን አስተዳደርና አመራር ዳይሬክተር ወ/ሮ አሰገደች መሬሳ በበኩላቸው ስልጠናው የአመራርነት አቅምን በመጨመር የትምህርት ቤቶቹን ቁልፍ ችግር ለመፍታት እንደሚያስችል ተናግረዋል፡፡
ስልጠናውንም ከዩኒቨርስቲዎች፣ ከመምህራን ኮሌጆችና ከክልልና የከተማ አስተዳደሮች የተመለመሉ አሰልጣኞች እንደሚሰጡት ተገልጿል።
ስልጠናው ከንድፈ ሀሳብ ይልቅ በተግባር ላይ ትኩረት ያደረገ እንደሚሆንም ተጦቁሟል።
ከዚህ ቀደም በናሙናነት በተመረጡ 40 ትምህርት ቤቶች ለሚገኙ የትምህርት አመራሮች ስልጠና መሰጠቱ ይታወሳል
Recent News
በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የምግብ ሜኑ ተመሳሳይ እንዲሆን ተወሰነ።
Dec 09, 2024
የእንግሊዝኛ ቋንቋ ክህሎትን ለማሳደግ በትኩረት መስራት እንደሚገባ ተጠቆመ።
Dec 07, 2024