News Detail
Oct 28, 2021
347 views
በዩኒቨርስቲዎች የሚነሳውን የትምህርት ጥራት ችግር ለማሻሻል ትኩረት ተሰጥቶ ሊሰራ እንደሚገባ ተገለፀ።
የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ከከፍተኛ ትምህርት አመራሮች ጋር ውይይት አካሄዱ።
በውይይቱም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን እና የትምህርት አሰጣጥ ሂደቱን ለማዘመን መንግስት ትኩረት እንደሚሰጥ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ተናግረዋል።
በ ዩኒቨርስቲዎቹም የአስተዳደር እና የመሰረተ ልማት ችግሮች እንደሚስተዋሉ ሚኒስትሩ አንስተዋል።
አብዛኛዎቹ ዩኒቨርስቲዎች ከትምህርት ጥራት ጋር በተያያዘ የሚነሳባቸውን ጥያቄዎች ለመመለስ እንዲችሉ ያሉባቸውን ክፍተቶች በአፋጣኝ ለይተው የመፍትሄ እርምጃዎችን እንዲወስዱም ሚኒስትሩ መመሪያም ሰጥተዋል።
በሌላ በኩል ዩኒቨርስቲዎች የፖለቲካ አቋም አራማጅ መሆን እንደሌለባቸውም አሳስበዋል።
ከመንግስት ተጽዕኖ ነጻ የሆነ አሰራር ለመዘርጋት ዩኒቨርስቲዎቹ ትኩረት አድርገው ሊሰሩ እንደሚገባም ገልፀዋል።
Recent News
በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የምግብ ሜኑ ተመሳሳይ እንዲሆን ተወሰነ።
Dec 09, 2024
የእንግሊዝኛ ቋንቋ ክህሎትን ለማሳደግ በትኩረት መስራት እንደሚገባ ተጠቆመ።
Dec 07, 2024