News Detail

የሀገር ውስጥ ዜና
Mar 30, 2020 661 views

በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ትምህርት መቋረጡን ተከትሎ ሊወሰድ ስለሚገባው ጥንቃቄ ሚኒስትሩ ገለፁ፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር ሚንስትር ክቡር ዶ/ር ኢንጂነር ጌታሁን መኩሪያ፣ በአለም አቀፍ ደረጃ በወረርሽኝነት የተፈረጀውን የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ 19) ስርጭት ለመግታት የቅድመ-መደበኛ፣ የአንደኛ እና ሁለተኛ ደረጃ እንዲሁም የጎልማሶች ትምህርት ተማሪዎች ሊያደርጉ ስለሚገባቸው ጥንቃቄዎች መግለጫ፡፡

ክቡር ዶ.ር ኢንጂነር ጌታሁን መኩሪያ አያይዘውም መንግስት የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት እስከ መጋቢት 21/2012 ዓ.ም ድረስ ለ15 ቀናት ትምህርት ቤቶች እንዲዘጉ ማድረጉን አስታውሰው የተዘጉትን የትምህርት ቀናት ለማካካስ ተማሪዎች ላይ ምንም ዓይነት ጫና ሳያድር፣ የትምህርት አመራሮች፣ መምህራንና ማህበረሰቡ በሚወጣው የጊዜ መርሃ-ግብር በመመራት ጊዜያቸውን በአግባቡ በመጠቀም እንደሚያካክሱ አሳውቀዋል፡፡ በተጨማሪም ሚኒስትሩ ሲገልፁ፣ የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና እና የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ተፈታኞች በተዘጉት የትምህርት ቀናት በቤታቸው ዝግጅታቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ አሳስበው፣ የፈተና ወቅት በተመለከተ መርሃ-ግብሩን ወደፊት እንደሚገለጽ አሳውቀዋል፡፡

Recent News
Follow Us