News Detail

የሀገር ውስጥ ዜና
May 07, 2021 264 views

በ499 ትምህርት ቤቶች የሚተገበረው የተማሪዎች የትምህርት ቤት ምገባ ፕሮግራም ይፋ ሆነ።

የትምህርት ሚኒስቴር ከህፃናት አድን ድርጅት /Save the children / ጋር በገባው ውል የተቀናጀ አካታች ሀገር በቀል የምገባ ፕሮግራም ማስጀመሪያ መርሃ ግብር በሲዳማ ብ/ክ/መንግስት አካሂዷል፡፡ የትምህርት ሚኒስቴር ደኤታ አቶ ሚሊዮን ማቲዎስ የተማሪዎች የምገባ ፕሮግራም አማራጭ ሳይሆን ትውልድን

ይህ የተማሪዎች የምገባ ፕሮግራም በመማር ማስተማሩ ሂደት የተማሪዎችን ተሳትፎ ከማሳደግ ባሻገር እንደ ሀገር ውጤታማና ንቁ ዜጎችን በፍትሃዊነት ለማፍራት የሚያግዝ መሆኑንም ሚኒስቴር ዴኤታው ገልፀዋል፡፡

የሀገር በቀል ምገባ ፕሮግራሙ በተለይም በተፈጥሮ እና ሰው ሰራሽ ችግር ምክንያት የተጎዱ ተማሪዎች የተመጣጠነ ምግብ እንዲያገኙና በትምህርታቸውም ውጤታማ እንዲሆኑ እንደሚያግዛቸውም ነው የተነገረው፡፡

የሲዳማ ክልል ም/ር/መስተዳድር እና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ በየነ በሪሶ በበኩላቸው የምገባ ፕሮግራሙ የትምህርት ቤቶችን ውስጣዊ ብቃት እና የተማሪዎችን ተሳትፎን  የሚያሳድግ መሆኑን ገልፀዋል።

ፕሮግራሙ በተለያየ ችግር ምክንያት ትምህርታቸውን አቋርጠው የነበሩ ወደ ትምህርት ቤት እንዲመለሱና ሌሎችም ትምህርታቸውን እንዳያቋርጡ ከማድረግና ፍትሃዊነትን ከማረጋገጥ አንፃር  ወሳኝ መሆኑም  ተነግሯል።

ፕሮግራሙ በክልሉ ውስጥ የተሳካ እንዲሆንና ቀጣይነት እንዲኖረው የክልሉ መንግስት የሚቻለውን ሁሉ ድጋፍ የሚያደርግ መሆኑንም  
ም/ር/መስተዳድሩ ተናግረዋል።

 የህፃናት አድን ድርጅት በኢትዬጵያ ዋና ዳይሬክተር ኢኪን ኦጉቶጉላሪ በበኩላቸው የተቀናጀ አካታች ሀገር በቀል የተማሪዎች ምገባ ፕሮግራም በ499 ትምህርት ቤቶች የሚተገበር መሆኑን እና የምገባ ፕሮግራሙ ህፃናት ትምህርታቸውን እንዳያቋርጡ የሚረዳ  መሆኑን ገልፀዋል፡፡

 የምገባ ፕሮግራሙን እውን ለማድረግም Global partnership for education በተሰኘ ግብረሰናይ ድርጅት  21.4 ሚሊየን ብር ድጋፍ መደረጉንም ዳይሬክተሩ ተናግረዋል።

የተቀናጀ አካታች ሀገር በቀል የተማሪዎች ምገባ ፕሮግራም በአምስት ክልሎች የሚተገበር ሲሆን በአጠቃላይ 499 በላይ ትምህርት ቤቶች እንዲሁም 163 ሺ በላይ ተማሪዎችን ተጠቃሚ ያደርጋል ተብሏል ፡፡

Recent News
Follow Us