News Detail

National News
Dec 03, 2020 755 views

የትምህርት መረጃና አስተዳደር ስርዓትን ለመሻሻል እየተሰራ ነው፡-ትምህርት ሚኒስቴር

የትምህርት መረጃና አስተዳደር ሥርዓትን ለማሻሻል እየተሰራ እንዳለ የሚኒስቴሩ የትምህርት መረጃና አስተዳደር ስርዓት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ተወካይ አቶ ሰብስብ ለማ ገልጸዋል፡፡

 

 

የትምህርት ሚኒስቴር የትምህርት መረጃ ስርዓት ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እቅዶች ጋር በተናበበ መልኩ የመረጃ መሰብሰቢያ ስርዓት

ለመዘርጋት የሚያስችል ‹‹የመረጃ መሰብሰቢያ ቋት›› ማሻሻያ በባለሙያዎች እየተዘጋጀ መሆኑን ዳይሬክተሩ ተናግረዋል፡፡

የሚሻሻለው የትምህርት መረጃ መሰብሰቢያ የነበሩትን በማስተካከልና አዳዲስ አሳቤዎችን በማካተት የሚዘጋጅ ይሆናል፡፡

እየተሰራ ባለው ማሻሻያ ላይ ከትምህርት ሚነስቴርና ከሁሉም ክልል ትምህርት ቢሮ የተውጣጡ የትምህርት መረጃና አስተዳደር ስርዓት ባለሙያዎች እየተሳተፉ ይገኛሉ፡፡

የሚሻሻለው የመረጃ መሰብሰቢያ ስርዓት እንደ ትምህርት ዘርፍ የሚስተዋለውን የመረጃ ስራዓት ችግር ይፈታል ተብሎ ይታመናል፡፡

Recent News
Follow Us