News Detail

National News
Jun 12, 2025 9 views

የሚኒስቴሩ ከፍተኛ አመራሮች የቡኢ ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ግንባታ የደረሰበትን ደረጃ ተመለከቱ።

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ እና የአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ አየለች እሸቴ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምስራቅ ጉራጌ ዞን ቡኢ ከተማ እየተገነባ የሚገኘውን ቡኢ የፌዴራል ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ግንባታ የደረሰበትን ደረጃ ተዘዋውረው ተመልክተዋል።
በዚሁ ጊዜ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የትምህርት ቤቱ ግንባታ በተያዘለት የጊዜ ገደብ ጥራቱን ጠብቆ በፍጥነት በማጠናናቀቅ በመጪው መስከረም የመጀመሪያውቹን ተማሪዎች መቀበል መጀመር አለበት ያሉ ሲሆን፤
ለዚህም ኮንትራክተሩ ኃላፊነቱን እንዲወጣ ጠይቀው በሚኒስቴሩ በኩል ከክፍያ ጋር የሚፈጠር ምንም አይነት መጓተት አይኖርም ብለዋል።
የፕሮጀክቱ ማናጀር እንዳለ ዘለቀ በበኩላቸው ግንባታው ጥራቱን ጠብቆ እየተከናወነ መሆኑን ጠቅሰው ሚኒስቴሩ ባስቀመጠው ጊዜ ውስጥ ተማሪዎችን ለመቀበል የሚያስችል ደረጃ ላይ ለማድረስ እየተሠራ እንደሚገኝም አብራርተዋል።
ትምህርት ሚኒስቴር በትምህርታቸው ብቁና ተወዳዳሪ የሆኑ ተማሪዎች ከመላ ሀገሪቱ ተመርጠው የሚገቡባቸው የፌዴራል ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች እያስገነባ እንደሚገኝም ይታወቃል።
Recent News
Follow Us