News Detail
Mar 13, 2025
76 views
የዩኒቨርሲቲ ሥራ አመራር ቦርድ አመራሮች የተሰጣቸውን ኃላፊነት በሚገባ እንዲወጡ ተጠየቀ፡፡ የዩኒቨርሲቲ ሥራ አመራር ቦርድ አባላት የምክክር መድረክ እየተካሄድ ይገኛል፡፡
በምክክር መድረኩ የተገኙት የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ እየተወሰዱ ባሉ የሪፎርም እርምጃዎች ዩኒቨርሲቲዎች ወደፊት ምን አይነት ደረጃ ላይ መድረስ እንዳለባቸው የሚያመላክቱ በመሆኑ የሥራ አመራር ቦርድ አመራሮች ዩኒቨርሲቲዎችን ለመቀየር እየተሄደበት ያለውን ሁኔታ አውቃችሁ በዛ ልክ ኃላፊነታችሁን ልትወጡ ይገባል ብለዋል፡፡
የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ኮራ ጡሽኔ በበኩላቸው የዩኒቨርሲቲ ሥራ አመራር ቦርድ አመራሮ ዩኒቨርሲቲዎች ካላቸው ራዕይና ተልዕኮ አንጻር የሰሯቸውን ሥራዎች በየጊዜው እየገመገሙ የተጠያቂነት ሥርዓትን መዘርጋት ይኖርባቸዋል ብለዋል፡፡
በተለይም የትምህርት ዘርፉን በመለወጥ ፍትሃዊና ጥራት ያለው ትምህርትን ለማረጋገጥ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንደሚያስፈልግም አብራርተዋል፡፡
በምክክር መድረኩ የዩኒቨርሲቲ አመራሮች ምልመላ፣ መረጣና ምደባ ፣ የከፍተኛ ትምህርት ረቂቅ አዋጅ እንዲሁም የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ነጻ የማህበረሰብ አገልግሎት ረቂቅ ሰነድ ለውይይት መነሻነት በከፍተኛ ትምህርት አስተዳደርና መሰረተ ልማት መሪ ሥራ አስፈጻሚ ሰለሞን አብርሃ (ዶ/ር) ቀርቧል፡፡
የቀረቡት ረቂቅ ሰነዶችም በከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ እየተተገበሩ ያሉ ሪፎርሞች የሚሄዱንበትን አቅጣጫ ህጋዊ መሰረት ለማስያዝ ያለመ መሆኑም ተገልጿል።
የቀረበውን ረቂቅ ሰነድ መነሻ በማድረግ የዩኒቭርሲቲ ሥራ አመራር ቦርድ አባላት የተለያዩ ጥያቄዎች አንስተው በሚመለከታቸው አካላት ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል፡፡
Recent News
የ3ኛ ዲግሪ ፕሮግራም ብቃት ማዕቀፍ ለትግበራ መሆኑ ተገለጸ፤
Mar 14, 2025
የትምህርት ሚኒስትሩ በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኧርቪን ማሲንጋ ጋር ተወያዩ፤
Mar 14, 2025