News Detail

National News
Mar 06, 2025 86 views

የትምህርት ሚኒስትሩ በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ወለጋ ዞን የሚገኙ ትምህርት ቤቶችን ጎበኙ።

የትምህርት ሚኒስትሩ ኘሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ወለጋ ዞን የሚገኙ ትምህርት ቤቶችን በመጎብኘት ተማሪዎችን አበረታተዋል።
በጉብኝታቸውም ገተማ ሁለተኛ ደረጃ እና የነጌሶ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤትን ተመልክተዋል።
በዚሁ ጊዜ ሚኒስትሩ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች አሁን ያሉበት ደረጃ የቀጣይ ህይወታቸው የሚወሰንበት በመሆኑ ጠንክራችሁ መማር ይጠበቅባችኋል፤ በፍፁም በጊዜ መቀለድ የለባችሁም ሲሉም አሳስበዋል።
ይህ ሀገር እንዲቀጥል የወደፊቱ ሀገር ተረካቢዎች እናንተ በመሆናችሁ በቀለም ብቻ ሳይሆን በስነ-ምግባርም የተመሰገናችሁ ልትሆኑ ይገባል ብለዋል።
አክለውም የሚቀጥለውን ትውልድ በመቅረፅ ረገድ ትልቁ ድርሻ የመምህሩ መሆኑን በማንሳት መምህራን የተሰጣቸውን ኃላፊነት በሚገባ እንዲወጡም ጠይቀዋል።
የኦሮሚያ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ቶላ በሪሶ (ዶ/ር) በበኩላቸው ተማሪዎች የዓመቱ ትምህርት በአግባቡ ስለማይሸፈንላቸውና ስታንዳርዱን የጠበቀ የክፍል ፈተና ስለማይወስዱ መጨረሻ እየተቸገሩ መሆኑን ጠቅሰው መምህራን በዚህ ረገድ ትኩረት ሰጥተው መስራትና ተማሪዎች ተገቢውን እውቀት ይዘው ከክፍል ክፍል እንዲዛወሩ ማድረግ እንዳለባቸው አሳስበዋል።
አመራሮቹ በትምህርት ቤቶቹ በነበራቸው ጉብኝት ሰላማዊ የመማር ማስተማር ስራ እየተከናወነ እንደሆነና ተማሪዎችም ተረጋግተው እየተማሩ መሆኑን መመልከት መቻላቸውን ገልፀዋል።
Recent News
Follow Us