News Detail
Oct 06, 2024
728 views
የትምህርት ሚኒስቴርና የዓለም ባንክ ከፍተኛ ስራ ሃላፊዎች ትምህርት ቤቶችን ጎበኙ
በትምህርት ሚኒስቴር የአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ አየለች እሸቴ በኢትዮጵያ የአለም ባንክ ዳይሬክተር ሜሪያም ሳሊም ጋር በመሆን በአዲስ አበባ ሁለት ት/ቤቶች ውስጥ ጉብኝት አካሂደዋል፡፡
የስራ ሀላፊዎቹ በወንድይራድና አፄ ናኦድ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤቶች ባካሄዱት ጉብኝት የመማር ማስተማር ስራው የሚከናወንባቸውን ስፍራዎች ጎብኝተዋል፡፡
ጉብኝቱን ተከትሎ ክብርት ሚኒስትር ዴኤታዋ ከመምህራንና የትምህርት አስተዳደር ባለሙያዎች ጋር ባደረጉት ውይይት መምህራኑ እና የትምህርት አስተዳደር ባለሙያዎች በጋራ በመሆን የተማሪዎችን ብቃት ለማሻሻልና የትምህርት ቤቶቹን የውስጥ አቅም ለማሳደግ እያደረጉት ላለው አስተዋጾ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡
ክብርት ወ/ሮ አየለች አክለው እንደገለጹት በመከናወን ላይ ያሉ ጅምር ስራዎች የተማሪዎችን ውጤት በማሻሻልና የትምህርት ቤቶቹን የውስጥ አቅም በመገንባት ረገድ በአጠቃላይ ለትምህርት ማህበረሰቡም ይሁን ለዘርፉ ተዋንያኖች መነሳሳትን የሚፈጥር በመሆኑ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ጠቁመዋል፡፡
በኢትዮጵያ የአለም ባንክ ዳይሬክተር ሜሪያም ሳሊም በበኩላቸው መምህራኑ እና የትምህርት አመራሩ ላይ አሁን የሚታየው ቁርጠኝነትና ተነሳሺነት የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ የሚያስችል መሆኑን በመግለጽ ለዚህም የአለም ባንክ ድጋፉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል፡፡
Recent News
በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የምግብ ሜኑ ተመሳሳይ እንዲሆን ተወሰነ።
Dec 09, 2024
የእንግሊዝኛ ቋንቋ ክህሎትን ለማሳደግ በትኩረት መስራት እንደሚገባ ተጠቆመ።
Dec 07, 2024