News Detail
Aug 02, 2024
1.5K views
ስርዓተ ትምህርቱ የአገሪቱን ተጨባጭ ሁኔታና ቀጣይ ጊዜያትን መሠረት ያደረገ መሆኑን የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ አስታወቁ።
የትምህርት ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማት አመራሮችና ሰራተኞች በዓመታዊ ዕቅድ አፈጻጸም ዙሪያ ውይይት አድርገዋል
የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ በውይይቱ ወቅት እንደገለጹት ሥርዓተ ትምህርቱ የአገሪቱን የአሁንና የመጪውን ጊዜ ፍላጎት ዝንዲሁም ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነትን ማዕከል የሚያደርግ መሆኑን ገልጸዋል።
የአንድ አገር ስርዓተ ትምህርት የአገርን የረጅም ጊዜ ጥቅም ማስጠበቅ የሚችሉ ዜጎች ማፍራት መሆኑንም ሚኒስትሩ ተናግረዋል። ሲቪል ሰርቫንቱም ከማንኛውም የፓለቲካ ፓርቲ ተጽእኖ ነጻ ሆኖ በችሎታውና በብቃቱ ብቻ ህዝብና አገረ መንግስትን ማገልገል እንደሚጠበቅበትም አስገንዝበዋል።
የትምህርት ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማት ሠራተኞችም የአገርና የህዝብን ጥቅም በማስጠበቅ ለተጀመሩ የለውጥና ዓበይት ስራዎች ውጤታማነት ሃላፊነታቸውን እንደሚወጡ መልዕክት አስተላልፈዋል።
በውይይቱ ወቅት የአጠቃላይ ትምህርት፣ የከፍተኛ ትምህርት፣ የኢትዮጵያ ትምህርት ባለስልጣንና የአገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ዕቅድ ከፈጻጸም ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።
በውይይቱ ላይ የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱና የየተቋማቱ ከፍተኛ አመራሮች እና ባለሙያዎች ተሳታፊ ሆነዋል።
Recent News
በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የምግብ ሜኑ ተመሳሳይ እንዲሆን ተወሰነ።
Dec 09, 2024
የእንግሊዝኛ ቋንቋ ክህሎትን ለማሳደግ በትኩረት መስራት እንደሚገባ ተጠቆመ።
Dec 07, 2024