News Detail
Jan 30, 2023
4.5K views
በ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና 50% እና በላይ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች ወደ ከፍተኛ ትምህርት እንደሚገቡ ተገለፀ፡፡
ጥር19/2015ዓም. (ትምህርት ሚኒስቴር) የትምህርት ሚኒስቴር የ2014 ዓ.ም 12ኛ ከፍል የዉጤት ትንታኔ፣ወደ ከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ውጤትና ተያያዥ ጉዳዮች አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል፡፡
መግለጫውን የሰጡት የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የተገኘው የፈተና ውጤት ከስርቆትና ከኩረጃ በፀዳ መልኩ በትክክል የተመዘገበ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
በ2014 ዓ.ም በተሰጠው ፈተና በሁለቱም የትምህርት መስክ ፈተናውን ከወሰዱት 896 ሺህ 520 ተማሪዎች ውስጥ 29 ሺህ 909 የሚሆኑት ተማሪዎች 50% እና በላይ ያስመዘገቡ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡
ከፍተኛ ውጤት የተበዘገበበት የትምህርት መስክ በተፈጥሮ ሳይንስ 666 ከ700 ከፍተኛ ውጤት ሆኖ የተመዘገበ ሲሆን በማህበራዊ ሳይንስ ደግሞ 524 ከ600 ከፍተኛ ውጤት ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
በክልሎች ደረጃ በዉጤት ደረጃ የጎላ ልዩነት እንደሌለ ገልፀው አዲስ አበባ፣ድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር እንዲሁም የሃረሪ ክልል የተሻለ ውጤት ያስመዘገቡ መሆኑን አብራርተዋል፡፡
በሃገር አቀፍ ደረጃ ፈተናውን ካስፈተኑ ትምህርት ቤቶች ውስጥ ሰባት ትምህርት ቤቶች ያስፈተኑትን ተማሪዎች 100% አሳልፈዋል ተብሏል፡፡
ወደ ዩኒቨርስቲ መግቢያ ውጤት ያላመጡ ተማሪዎች በማጠናከሪያ (remedial) ፕሮግራም እንደ ዩኒቨርስቲዎቹ የመቀበል አቅም ተማሪዎችን ውጤት መሰረት አድርጎ በሚጸም የምልመላ መስፈርት ለዚህ ዓመት ብቻ ወደ ዩኒቨርስቲዎች ገብተው በልዩ ሁኔታ በደከሙባቸው የትምህርት ዓይነቶች የተሻለ ዉጤት እንዲያስመዘግቡ የሚያስችል ድጋፍ ተደርጎላቸዉ ፈተና ተፈትነው የሚያልፉ ተማሪዎች የከፍተኛ ትምህርታቸውን እንድቀጥሉ ይደረጋል ብለዋል፡፡
የዚህ አመት የፈተና አንድምታ ለዓመታት ሲንከባለል የቆ የበርካታ ችግሮች መገለጫ እና ተሸፋፍኖ የቆየውን እውነተኛ የትምህርት ስርዓታችን ያለበትን ደረጃ ያመላከተ መሆኑን የሚያሳይ ሲሆን ለዚህም ሁሉም የትምህርት ባለድርሻ አካላት በጋር የሚወስዱት ሀላፊነት በመሆኑ ለቀጣይ ስራ መረባረብ ይገባል ብለዋል፡፡
Recent News
በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የምግብ ሜኑ ተመሳሳይ እንዲሆን ተወሰነ።
Dec 09, 2024
የእንግሊዝኛ ቋንቋ ክህሎትን ለማሳደግ በትኩረት መስራት እንደሚገባ ተጠቆመ።
Dec 07, 2024