News Detail

National News
Nov 30, 2022 3.7K views

ተማሪዎችን በተጓዳኝ ትምህርቶች ማሳተፍ በየዝንባሌያቸው እንዲያተኩሩ እንደሚያስችል ተጠቆመ።

በትምህርት ሚኒስቴር የቋንቋና ተጓዳኝ ትምህርቶች ስርዓተ ትምህርት ዴስክ ኃላፊ ወ/ሮ አስቴር በርሄ በተጓዳኝ ትምህርት ዙሪያ በተዘጋጀ ስልጠና ላይ እንደገለጹት ተጓዳኝ ትምህርቶች የተማሪዎችን ችሎታና ልዩ ተሰጥኦ ለማውጣት ያግዛል።
የተማሪዎች በተጓዳኝ ትምህርት የነቃ ተሳትፎ ማድረጋቸው የአዲሱን ስርዓተ ትምህርት ጽንሰ ሀሳብ ተረድተው ወደ ተግባር እንዲለውጡ እንደሚያስችላቸውም ጠቁመዋል።
በመሆኑም ተማሪዎችን ከመደበኛው ትምህርት ባሻገር በተጓዳኝ ትምህርቶች በማሳተፍ ችሎታቸውን አውጥተው እንዲጠቀሙ ማድረግ እንደሚገባ ወ/ሮ አስቴር ተናግረዋል
የተጓዳኝ ትምህርቶች ስርዓተ-ትምህርት ባለሙያ አቶ ሀብታሙ ገርቢ በበኩላቸው በተጓዳኝ ትምህርቶች አማካኝነት ተማሪዎች እውቀታቸውን አመለካከታቸውንና የህይወት ክህሎታቸውን በማሳደግ ድንበር ተሻጋሪ የባህል ግንኙታቸውን እንዲያዳብሩ አስተዋጽኦ እንደሚያደርግ ገልጸዋል።
ተጓዳኝ ትምህርቶች የመደበኛ ስርዓተ ትምህርት አካል ባይሆኑም ከመደበኛው ትምህርት ጋር የሚተሳሰሩና በትምህርት አመራር፣ በመምህራን፣ በተማሪዎችና ወላጆች ንቁ ተሳትፎ የሚተገበሩ ልዩ ልዩ ክበባትን ያጠቃልላል።
በስልጠናው ላይ የክልል ትምህርት ቢሮ ባለሙያዎች ፣ርዕሳነ መምህራንና ጉዳዩ የሚመለከታቸው መምህራን ተሳታፊዎች ሆነዋል።
Recent News
Follow Us