News Detail
Nov 30, 2022
3.5K views
አካታችና የስርዓተ ፆታ እኩልነትን ያረጋገጠ ውጤታማ የትምህርት ስርዓት መፍጠር እንደሚገባ ተገለጸ፡፡
ህዳር15/2015 ዓም. (ትምህርት ሚኒስቴር) የትምህርት ሚኒስቴር ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ አካቶ ትግበራ ስራ አስፈፃሚ ከብሪቲሽ ካውንስል ጋር በመተበባር አካታችና የሴቶች እኩልነትን ያረጋገጠ ውጤታማ ትምህርት በሚል ርዕስ ከሁሉም ክልሎች፣ ከተማ አስተዳደሮች እና መምህራን ኮሌጆች ለተውጣጡ መምህራን የ
ስልጠናውን በንግግር የከፈቱት የትምህርት ሚኒስቴር ስራ አመራር ዋና ስራ አስፈፃሚ ተወካይ ዶ/ር ኤዶሳ ተርፋሳ አካታችና የስርዓተ ፆታ እኩልነትን ያረጋገጠ ውጤታማ የትምህርት ስርዓት መፍጠር እንደሚገባ ተናግረው ትምህርት ሚኒስቴርም ይህንኑ ለማረገገጥ በርካታ ስራዎች እየሰራ እንዳለ ጠቁመዋል፡፡
ሚኒስቴሩ ልዩ ፍላጎትን ታሳቢ ያደረገ አካታች ውጤታማ ትምህርት በሁሉም ዘርፍ ከቅድመ አንደኛ እስከ ከፍተኛ ትምህርት ለማሻሻል የሚያስችሉ ፖሊሲዎችንና ስትራቴጂዎችን በማውጣት ተግባራዊ እያደረገ እንደሚገኝም አብራርተዋል፡፡
የሴቶችና አካቶ ትምህርት ውጤታማነትን ለማረጋገጥ ከመናገር በዘለለ በተግባር ማረጋገጥ ይገባል ያሉት ዶ/ር ኤዶሳ ለውጤታማነቱ ሁሉም በየደረጃው የሚገኝ ባለድርሻ አካል የድርሻውን ሊወጣ ይገባል ብለዋል፡፡
በመጨረሻም የሚሰጠው ስልጠና በሴቶችና አካቶ ትምህርት የተጀመሩ ተግባራት ወደ ኋላ እንዳይመለሱ ከፍተኛ እገዛ እንደሚኖረው ተናግረው ሰልጣኞች ወደ የመጡበት አካባቢ ሲመለሱ በትክክል ወደ መሬት ማውረድና አቻዎቻቸውን በማሰልጠን ተግባራዊነቱን መከታተል እንደሚኖርባቸው አሳስበዋል፡፡
የብሪቲሽ ካውንስል የአፍሪካ ሪጅናል ትምህርት ዘርፍ ካንትሪ ዳይሬክተር አቶ አሎ በበኩላቸው ብሪቲሽ ካውንስል በኢትዮጵያ በትምህርቱ ዘርፍ በርካታ ተግባራትን ከመንግስት ጋር በመተባበር እየሰራ እንዳለ ገልፀው እየተሰጠ ያለው የአሰልጣኞች ስልጠና አካታችና ፆታ እኩልነትን በትምህርቱ ዘርፍ ከማረጋገጥ አንፃር ያለውን አመለካከት ችግር ለማስተካከል ይረዳል ብለዋል፡፡
በትምህርት ሚኒስቴር የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ አካቶ ትግበራ ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ምህረተክርስቶስ ታምሩ በበኩላቸው ከምንናገረው በላይ በየትምህርት ቤቶቻችን ምቹ ሁኔታዎችን በመፍጠር ሁሉም ዜጎች እኩል የሚማሩበት የትምህርት ስርዓት መፍጠር አለበን ብለዋል፡፡
የአሰልጠኛች ሰልጠናው ሲጠናቀቅ ሰልጣኞች ወደ የመጡበት በመመለስ በስራቸው ያሉትን የሚያሰለጥኑ መሆኑ ታውቋል፡፡