News Detail
Nov 21, 2022
3.5K views
የትምህርት ቤቶችን ደረጃ ለማሻሻል በትኩረት መስራት እንደሚገባ ተገለፀ።
የአጠቃላይ ትምህርት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ፋንታ ማንደፍሮ( ዶ/ር ) የትምህርት ቤቶችን ደረጃ ለማሻሻል ሁሉም ክልሎች በትኩረት መስራት እንደሚገባቸው ገልጸዋል ።
በተለይም የመማር ማስተማር ስራው የትምህርት ጥራትን ባረጋገጠ መልኩ መስራትና በቴክኖሎጂ ማስደገፍ እንደሚገባ አሳስበዋል።
አክለውም የመምህራንን ብቃት ለማሻሻል ከዚህ ቀደም ከሚሠራው አሰራር በመውጣት በልዩ ትኩረት መስራት እንደሚገባ ተናግረዋል።
በትምህርት ዘርፉ የሚስተዋለውን የጥራት ችግር ለመቅረፍ ሁሉንም ባለድርሻ አካላት ማሳተፍና በአጭር ጊዜ ማረጋገጥ እንደሚገባም ተገልጿል።
በአጠቃላይ ትምህርት ዘርፍ ሲካሄድ የነበረው የጎንዮሽ ውይይት ባለ 7 ነጥብ የአቋም መግለጫ በማውጣት ትናንት ማምሻውን ተጠናቋል።
ዋናው ጉባኤ በዛሬው እለት ሁለቱም የትምህርት ዘርፎች ፣የክልል ት/ቢሮ ሃላፊዎች፣ የዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንቶች ፣ የትምህርት አጋር ድርጅቶች ፣ ባለድርሻ አካላት እና ሌሎች እንግዶች በተገኙበት ይካሄዳል።