News Detail

National News
Nov 21, 2022 3K views

በአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እየተደረገ ያለው የትምህርት ቤት ምገባ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ(ፒኤችዲ) አስገነዘቡ፡፡

ህዳር 6/2015ዓም (ትምህርት ሚኒስቴር) በአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እየተደረገ ያለው የትምህርት ቤት ምገባ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ(ፒኤችዲ) ገልጸዋል ።
በዚህ ዓመት ከ200ሺ በላይ ተጨማሪ ተማሪዎችን መመገብ የሚያስችል አቅም መፈጠሩንም ጠቁመዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬ ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች በሰጡት ማብራሪያ በትምህርት ቤት ምገባ መርሀ ግብር እየተከናወነ ያለው ስራ የሚያስደስትና ሊኮራበት የሚገባው ነው ብለዋል።
በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ዘጠን ነጥብ አምስት ሚሊዮን ተማሪዎች በቀን ሁለት ጊዜ በትምህርት ቤት መመገብ መቻሉን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አብራርተዋል፡፡
በዚህም ባለፈው ዓመት ከነበረው ዘጠኝ ነጥብ አራት ሚሊዮን ተማሪዎች ቁጥር ጋር ሲነጻጸር ከሁለት መቶ ሺህ በላይ ተማሪዎች መጨመር የሚያስችል አቅም መፈጠሩን አመላክተዋል፡፡
የሁሉ ነገር መሰረት በሆነው የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎችን መመገብ በምግብ እጦት ምክንያ ነገ ሳይንቲስቶች ፣ ሀኪሞችና ኢንጂነሮች ሊሆኑ የሚችሉ ተማሪዎች ትምህርት እንዳይስተጓጎል መርዳት መሆኑንም አስታውሰዋል፡፡
የትምህረት ቤት ምገባ መርሀ ግብሩ ከኑሮ ውድነቱ ጋር በተያያዘ ልጆቻቸውን ትምህረት ቤት መላክ ያልቻሉ ወላጆችን መደገፍ ጭምር መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስገንዝበዋል፡፡
በመሆኑም በአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እየተካሄደ ያለው የተማሪዎች ምገባ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባም ጠቅላይ ሚኒስትሩ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ማብራሪያው አሳስበዋል፡፡
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
Recent News
Follow Us