News Detail
በጦርነቱ የተጎዱ የትምህርትና የጤና ተቋማትን በተሻለ ሁኔታ መልሶ ለመገንባት የሚያስችል የስምምነት ሰነድ ተፈረመ፡፡
የስምምነት ሰነዱም የሦስቱ ተቋማት አመራሮች በተገኙበት በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የመሰብሰቢያ አዳራሽ ተፈርሟል፡፡
የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በጦርነቱ ከወደሙ 1,300 ት/ቤቶች መካከል 200 የሚሆኑትን በዚህ በጀት ዓመት በተሻለ ሁኔታ ሰርቶ ለትምህርት ክፍት ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ጠቅሰው ዲያስፖራው ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው “አይዞን ኢትዮጵያ” ፕላትፎርም በኩል ተሳትፎውን አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል።
አክለውም ዳያስፖራው ለሀገሩ የሚያወጣው ገንዘብ ለታለመለት አላማ ብቻ ይውላልም ብለዋል፡፡
የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ በበኩላቸው በግጭት የተጎዱ ተቋማትን መልሶ ለመገንባት በዚህ መልኩ ስምነቶችን መፈራም መቻሉ ስራዎችን በተደራጀ መልኩ ለማከናወን ትልቅ አቅም እንደሚሆን ገልፀዋል፡፡
የኢትዮጵያ ዳያስፖራ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር መሐመድ እንድሪስ በውጭ ሀገራት ያለው ዳያስፖራ ሀገሩን በተለያየ አግባብ ሲረዳ የቆየ ቢሆንም ሥርዓት ዘርግቶና በተደራጀ መልኩ ተሳትፎ እንዲያደርግ ማድረግ አስፈላጊ በመሆኑ “የአይዞን ኢትዮጵያ” የሚል ፕላትፎርም መመስረቱን ጠቀሰዋል፡፡
በመሆኑም ዳያስፖራው በተፈጠረው የአይዞን ኢትዮጵያ ፕላትፎርም ተጠቅሞ ድጋፉን አጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል፡፡
Recent News
Sep 02, 2025
Aug 29, 2025
Aug 28, 2025
Aug 23, 2025