News Detail
Aug 16, 2022
2.9K views
የከፍተኛ ትምህርት የመውጫ ፈተና ማስፈፀሚያ መመሪያ ፀደቀ።
የከፍተኛ ትምህርትን አገራዊ ቅድመ ምረቃ የመውጫ ፈተናን በአግባቡ ለመምራትና ለማስተዳደር የተዘጋጀው የከፍተኛ ትምህርት መውጫ ፈተና ማስፈፀሚያ መመሪያ ፀድቋል።
መመሪያው በፍትህ ሚኒስቴር ተመዝግቦ እና ፀድቆ ለትግበራም ይፉ ሆኗል።
መመሪያው በመውጫ ፈተና ዝግጅት ሊካተቱ ስለሚገባቸው ሃገራዊ ዝቅተኛ የትምህርት ብቃት መመዘኛዎችን ፣ የሙያ ሥነምግባር ደምቦችን እና ተቋማት ሊከተሏቸው የሚገቡ የአሠራር ስነ- ስርዓቶችን አካቷል ።
መመሪያው የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅና ሀገሪቱ የምትፈልገውን የሠለጠነ የሠው ሀይል ለማፍራት ከሚደረጉ ማስፈፀሚያ ስልቶች አንዱ ነው።
በመመሪያው ዝግጅት ሂደት ውስጥ በስርዓተ ትምህርት እና ፈተና ዝግጅት ከፍተኛ ልምድ ያካበቱ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ምሁራን፣የሙያ ማህበራት ተወካዮች እንዲሁም ሌሎች ባለድርሻ አካላት አስፈላጊውን ግብአት ሰጥተውበታል ።
የፀደቀው መመሪያ ከሚቀጥለው የትምህርት ዘመን ጀምሮ ተግባራዊ እንዲሆን ለሁሉም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተልኳል።
Recent News
Sep 02, 2025
Aug 29, 2025
Aug 28, 2025
Aug 23, 2025