News Detail

National News
Apr 18, 2022 5.6K views

በጦርነትና ግጭት ውስጥ ሆነው የተፈተኑና የማለፊያ ነጥብ ያላመጡ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ከ2014 ዓ.ም መደበኛ ተፈታኞች ጋር እንዲፈተኑ ውሳኔ ተላለፈ።

ትምህርት ሚኒስቴር ከክልል እና ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮዎች ጋር ተከታታይ ውይይት በማድረግ የተለያዩ ውሳኔዎችን አሳልፏል።
በመግለጫው የ2013ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና እርማት በተመለከተ ያጋጠመ ችግር አለመኖሩን ሚኒስቴሩ አስታውቋል።
በአብዛኞቹ ክልሎች ያጋጠመ የውጤት መቀነስ መኖሩን እና ትምህርት ሚኒስቴር አማራጮችን የማየት ስራ መስራቱንም በመግለጫው ተነስቷል።
በዚህም በጦርነትና ግጭት ውስጥ ሆነው የተፈተኑ አካባቢዎች እና የማለፊያ ነጥብ ያላመጡና ወደ መንግስት ዩኒቨርስቲ መግባት ያልቻሉ ተማሪዎች በ2014ዓ.ም በሚሰጠው የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና እንደ መደበኛ ተማሪ እንዲፈተኑ ውሳኔ ተላልፏል።
ከዩኒቨርስቲዎች ጋር ውይይት በማድረግ ተጨማሪ የቅበላ አቅም እንዲኖር ከስምምነት ላይ መደረሱን እና ተጨማሪ የቅበላ አቅም በፍትሀዊነት በጦርነቱ ምክኒያት ለተጎዱ ክልሎችእንዲከፋፋል ውሳኔ ተላልፏል።
የፈተና ውጤት ማሳወቅን በተመለከተም በሁለት ዙር ፈተና በመሰጠቱ አጋጥሞ የነበረው ችግር መታረሙ በመግለጫው ተገልጿል።
በመጀመሪያው ዙር ተፈታኞች በስነ-ዜጋ ትምህርት ካጋጠመዉ ችግር ውጪ ሌሎች ችግሮች ባለማጋጠማቸው የሌሎች ትምህርት ዓይነቶችን ውጤት ውድቅ ለማድረግ አሳማኝ የውጤት ትንተና አለመኖሩም ነው የተገለፀው ።
በመንግስት ዩኒቨርስቲዎች ቅበላ የሚያገኙትን በተመለከተ በቀደምት ዓመታት ከመሰናዶ ትምህርት በኋላ ከሚፈተኑ ጋር በማነፃፀር የተፈጠረ አለመረዳት መኖሩንም ሚኒስቴሩ ገልጿል።
በቀጣይም እንደዚህ አይነት ችግሮች እንዳይፈጠሩ የተጠናከረ ስራ ለመስራት ከስምምነት ላይ መደረሱ ተገልጿል።
Recent News
Follow Us