News Detail

National News
Mar 28, 2022 2.2K views

በአፋር ክልል በጦርነቱ ምክንያት በተማሪዎችና በመምህራን ላይ የሚፈጠሩ ስነልቦናዊና ማህበራዊ ጉዳቶችን ለመቅረፍ የሚያስችል የአሰልጣኞች ስልጠና እየተሰጠ ነው።

ትምህርት ሚኒስቴር በአፋር ክልል በጦርነቱ ምክንያት በተማሪዎችና በመምህራን ላይ የሚፈጠሩ ስነልቦናዊና ማህበራዊ ጉዳቶችን ለመቅረፍ የሚያስችል የአሰልጣኞች ስልጠና እየሰጠ ይገኛል።
የስልጠናው ዓላማም በጦርነቱ ምክንያት የተጎዱ ህጻናትና ተማሪዎች አእምሯዊና ማህበራዊ ችግር እንዳይገጥማቸውና ትምህርታቸውን በአግባቡ መከታተል የሚችሉበትን ሁኔታ ለመፍጠር ያለመ መሆኑ ተገልጿል ።
በአሁን ሰዓት በክልሉ በጦርነት ከተጎዱ ወረዳዎች የተውጣጡ 50 መምህራን ስልጠናውን እየተሳተፉ ይገኛሉ።
በትምህርት ሚኒስቴር የመምህራን ልማት ከፍተኛ ባለሙያ አቶ ተስፋዬ ደገፋው ከተማሪዎች በተጨማሪ መምህራኑም ራሳቸው በጦርነቱ የተጎዱ በመሆናቸው ችግር ሳይገጥማቸው ተማሪዎችን በአግባቡ ማስተማር እንዲችሉ የአሰልጣኞች ስልጠናው እንደሚያግዝ ገልፀዋል።
የአፋር ክልል ትምህርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ደረሳ መሀመድ በበኩላቸው የአሰልጣኞች ስልጠናው በክልሉ በጦርነቱ ምክንያት የተጎዱ ተማሪዎች መምህራንና ተማሪዎችን ስነ ልቦናዊና ማህበራዊ ድጋፍ እንዲያገኙ እንደሚያስችል ገልጸዋል።
ስልጠናውም በአሰልጣኞች ስልጠና ተሳታፊዎች አማካኝነት እስከታች ወርዶ እንደሚሰጥ ተገልጿል።
Recent News
Follow Us