News Detail
Feb 11, 2022
495 views
የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች የትምህርት ሚኒስቴርን ጥሪ ተቀብለው በጦርነቱ ለተጎዱ ትምህርት ተቋማት የሚሆን ድጋፍ እያደረጉ ነው።
የትምህርት ሚኒስቴር የወደሙ ትምህርት ተቋማትን መልሶ ለመገንባት የያዘው እቅድ አካል የሆነው የድጋፍ ማሰባሰብ ስራ በተቋሙ መግቢያ 4ኪሎ አደባባይ ፊት ለፊት እየተካሄደ ይገኛል።
ይህንንም ተከትሎ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ለወደሙ ትምህርት ተቋማት የሚሆን የደብተር፣ እስኪብርቶ፣ መርጃ መፀሐፍት እና ለነዋሪዎች የሚሆን የአልባሳት ድጋፍ በቦታው በመገኘት እያደረጉ ነው።
ድጋፍ የማሰባሰብ ዘመቻውም ለሁለት ሳምንታት የሚቀጥል ይሆናል።
ከዚህ በተጨማሪም በአጭር የፅሁፍ መልዕክት 9222 ላይም ማህበረሰቡ የሚፈልገውን የብር መጠን በቁጥር እየፃፈ በመላክ ድጋፍ የማሰባሰብ ስራም ተጀምሯል።
ህብረተሰቡም የወደሙ ትምህርት ተቋማትን መልሶ ለመገንባት የሚደረገውን እንቅስቃሴ በቻለው አቅም እንዲደግፍ የትምህርት ሚኒስቴር ጥሪ ያቀርባል።