News Detail
Oct 06, 2021
1K views
20 ሺ የተማሪዎች ቦርሳ ድጋፍ ተደረገ።
የቻይና ፋውንዴሽን ከአሊባባ ጋር በመተባበር 20 ሺ የተማሪዎች ቦርሳ ለትምህርት ሚኒስቴር ድጋፍ አደርጓል።
ድጋፉ 118 ሺ ቦርሳዎችን ለመደገፍ ቃል ከተገባው ውስጥ የመጨረሻው ዙር ነው።
የትምህርት ሚኒስትሩ ጌታሁን መኩሪያ (ዶ/ር ኢንጂ.) የቻይና መንግስት የኮቪድ ወረርሽኝ ከተከሰተበት ጊዜ ጀምሮ የህክምና ባለሙያዎችን ከመላክ ጀምሮ እስከ ክትባት ድረስ ከፍተኛ ድጋፍ ሲያደርግ መቆየቱን ተናግረዋል።
በትምህርት ዘርፉ በኩል ደግሞ ከ300ሺ በላይ ለሚሆኑ መምህራን የሚሆን ክትባት ድጋፍ ማድረጉን ያነሱት ሚኒስትሩ ለተማሪዎች ስለተደረገው ድጋፍም ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
በኢትትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ዋና ፀሃፊ ኬ ሊዮ ቻይና ከድህነት ወጥታ በአለም በኢኮኖሚ መሪ ከሆኑ ሀገራት ተርታ የተሰለፈችው ለትምህርት ልዩ ትኩረት በመስጠቷ ነው ብለዋል።
በመሆኑም ኢትዮጵያ በትምህርት ዘርፍ በምትሰራቸው ስራዎች ቻይና ድጋፏን አጠናክራ ትቀጥላለች ብለዋል።
ድጋፉ በተለያዩ ክልሎች ለሚገኙ ተማሪዎች የሚከፋፈል ሲሆን የኦሮምያና የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮዎች ድጋፉን ተረክበዋል።
የሌሎች ክልሎች ትምህርት ቢሮዎችም በቀጣይ ድጋፉን ተረክበው የሚያከፋፍሉ ይሆናል።
Recent News
በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የምግብ ሜኑ ተመሳሳይ እንዲሆን ተወሰነ።
Dec 09, 2024
የእንግሊዝኛ ቋንቋ ክህሎትን ለማሳደግ በትኩረት መስራት እንደሚገባ ተጠቆመ።
Dec 07, 2024