News Detail

National News
Jun 03, 2021 330 views

የትምህርት ሚኒስቴር የሂሳብና የሳይንስ ትምህርትን ለማሻሻል የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ

የትምህርት ሚኒስቴር Minimum learning competence Ethiopia ከተባለ አገር በቀል ድርጅት ጋር በሂሳብና በሳይንስ ትምህርት በጋራ ለመስራት የሚያስችል የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረሟል፡፡

የመግባቢያ ስምምነቱን የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ደኤታ ገረመው ሁሉቃ(ዶ/ር) እና የ Minimum learning competence Ethiopia ዋና ዳይሬክተር አቶ ዘላለም ደምሴ ተፈራርመዋል፡፡

የመግባቢያ ስምምነቱ የሂሳብና የሳይንስ ትምህርት በቴክኖሎጂ የተደገፈ እንዲሆን የአሰራር ማሻሻያ በማድረግ የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ እንደሚያስችል ተመልክቷል፡፡

 ስምምነቱ  በቴክኖሎጂ የተደገፉ አዳዲስ አሰራሮችን በመተግበር በሳይንስ ፣ በቴክኖሎጂ ፣ በኢንጅነሪንግ እና በሂሳብ ትምህርቶችን ለማሻሻል ያስችላል ተብሏል።

የሂሳብና የሳይንስ ትምህርት ፈጠራዎችን በቴክኖሎጂ አሰራር በመደገፍ ለተማሪዎች ፍላጎትና ዝንባሌ አጽንኦት እንደሚሰጥ በስምምነቱ ተጠቅሷል።

ለሂሳብና የሳይንስ ትምህርት ጤናማ አካባቢን በመፍጠር ለመጀመሪያና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ምቹ የጥናትና የመማሪያ ቦታዎች መፍጠር እና የሂሳብና የሳይንስ ትምህርት መምህራን የማስተማር ክህሎት ማሳደግም የመግባቢያ ስምምነቱ አንዱ አካል ነው።

የትምህርት ሚኒስቴር የትምህርት ዘርፉን በቴክኖሎጂ ለመደገፍ የተለያዩ ስራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝ መግለፁ ይታወሳል።

Recent News
Follow Us