News Detail

National News
Feb 25, 2021 252 views

ኢትዮጵያ ኮቪድ 19ኝን በመከላከል የመማር ማስተማር ስራዋን ያስቀጠለችበትን ተሞክሮ ለአለም አቀፉ የትምህርት ውይይት መድረክ አቀረበች።

ኢትዮጵያ የተለያዩ ሀገራት የትምህርት ሚኒስቴሮች በተሳተፉበት የአለም አቀፉ የትምህር ውይይት ላይ ተሳትፋለች።

በውይይቱ የኮቪድ 19ኝ ወረርሽኝን በመከላከል የመማር ማስተማሩን ሂደት ማስቀጠል መቻሏን አብራርታለች። 

በውይይቱ የተሳተፉት የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታው ገረመው ሁሉቃ (ፒ ኤች ዲ) ትምህርት ቤቶች በተዘጉበት ወቅት የመማር ማስተማር ስራውን በቴክኖሎጂ በመደግፍ ማስቀጠል መቻሉን ተናግረዋል። 

ትምህርት ቤቶች ዳግም ሲከፈቱም ከጤና ሚኒስቴር ጋር በመተባበር በትምህርት ቤቶች የሚተገበር የኮቪድ መከላከል ፕሮቶኮል በማዘጋጀት፣ ማህበረሰቡን ያሳተፈ "ወደ ትምህርት ቤት እንመለስ" ንቅናቄን በማድረግ መማር ማስተማር ስራውን ማስቀጠሏን አብራርተዋል። 

የተለያዩ ሀገራት ዳግም ትምህርት ቤቶችን ለመዝጋት ሲገደዱ ኢትዮጵያ ግን ማህበረሰብን ባሳተፈ ስራዋ ውጤታማ ስራ መስራቷ ተጠቅሷል። 

የትምህርት ውይይቱ በትምህርት ዘርፍ በቀጣይ ሊደረጉ ስለሚችሉ ጥንቃቄዎች የልምድ ልውጥ ለማድረግ ታስቦ የተዘጋጀ ነው። 

በውይይቱ የትምህርት ዘርፍ የሰው ሃይል ልማት፣ ዝቅተና ገቢ ላላቸው ሰዎች፣ ለሴቶችና ልዩ ፍላጎት ላላቸው ትምህርትን በፍትሃዊነት ማዳረስ ላይም መክረዋል።

Recent News
Follow Us