News Detail
Jan 23, 2021
514 views
"ሴቶች ለመብታቸው መታገል አለባቸው" :- ክብርት ወ/ሮ ሁሪያ አሊ
የትምህርት ሚኒስቴር የአስተዳደር ሰራተኞች የህይወት ክህሎት ተሞክሮ ለማዳበርና ከተለያዩ ጾታን መሰረት ካደረጉ ጥቃቶንና ጎጂ ልምዶችን ራሳቸውንና ሌሎችንም እንዲከላከሉ የ ምክክር መድረክ አካሄደ፡፡
በመድረኩ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የትምህርት ጥራት ማረጋገጥ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ ሁሪያ አሊ ያሳለፉትን የትምህርት ዘመን ተሞክሮኣቸውን ለተሳታፊዎች አቅርበዋል።
ሚኒስትር ዴኤታዋ በማህበራዊ፣ በኢኮኖሚያዊና በፖሊቲካዊ ጉዳዮች ዙሪያ ሴቶችን ያላሳተፈ ሥራ ውጤት ለማምጣት እንደማይቻል አስረድተዋል፡፡
በትምህርት ሚኒስቴር የሴቶች ሕፃናትና ወጣቶች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ የሺሃረግ ነጋሽ በበኩላቸው የመድረኩ ዓላማ የአስተዳደር ሰራተኞች የህይወት ክህሎት ተሞክሮ ለማዳበርና ከተለያዩ ጾታን መሰረት ካደረጉ ጥቃቶንና ጎጂ ልምዶችን ራሳቸውንና ሌሎችንም እንዲከላከሉ ለማስቻል እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
ፆታን መሰረት ያደረገ ጥቃት መነሻው በማህበረሰቡ ዘንድ የሚስተዋሉ አድሎአዊ በሴቶችና ወንዶች መካከል የተፈጠረ የስርዓተ ፆታ አመለካከት መዛባት መሆኑንም ተጠቅሷል።
በመድረኩ የክብርት ወ/ሮ ሁሪያን ጨምሮ በተጋባዥ እንግዶች የህይወት ዘመን ክህሎት ቀርቦ በተሳታፊዎች ውይይት ተደርጎበታል፡፡