News Detail

National News
Feb 16, 2026 19 views

በአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት መሠረት ለአይነ ስውራን የተዘጋጁ የ2ኛ ደረጃ የብሬል መጽሐፍት እየተጓጓዙ ነው።

የአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ አየለች እሸቴ በመጀመሪያው ዙር ለስርጭት የተዘጋጁ የብሬል መጽሀፍቱን የስርጭት ሂደት ተመልክተዋል።
‎ክብርት ሚኒስትር ዴኤታዋ የመጽሐፍቱን ስርጭት ሂደት ምልከታ ባደረጉበት ወቅት እንደገለጹት የትምህርት ጥራት፣አግባብነት ፣ፍትሃዊነትና ተደራሽነትን ለማረጋጥ የተለያዩ የሪፎርም ስራዎች ተግባራዊ እየተደረጉ ይገኛል ብለዋል።
‎ከሪፎርም ስራዎች መካከልም የተሻሻለውን የትምህርትና ስልጠና ፖሊሲ መነሻ በማድረግ አዲስ ስርዓተ ትምህርት ተቀርጾ ተግባራዊ መደረጉን ክብርት ሚኒስትር ዴኤታ ገልጸዋል።
‎ተግባራዊ በተደረገው ሥርዓተ ትምህርት መሠረትም ተማሪዎችና መምህራን የሚገለገሉባቸውን የመማሪያና የማስተማሪያ መጽሀፍት አንድ ለአንድ ለማድረስ ሲሰራ መቆየቱንም ክብርት ወ/ሮ አየለች ተናግረዋል።
‎ሁሉም ዜጎች የመማርና የመማሪያ ግብዓቶችን ማግኘት መብት እንዳላቸው ያስገነዘቡት ክብርት ሚኒስትር ዴኤታ ዜጎች በሁሉም ረገድ እኩል የትምህርት እድል ማግኘት እንዲችሉ እየተሰራ መሆኑንም ጠቅሰዋል።
‎ለስርጭት የተዘጋጁት የብሬል መጽሐፍት አይስውራን ተማሪዎች በቂ የመማሪያ መጽሐፍት አግኝተው ራሳቸውን በማብቃት ከሌሎች ተማሪዎች ጋር እኩል እድል እንዲያገኙና በእውቀትና በክህሎት ብቁ ሆነው እንዲገኙ እንደሚያስችሉ ገልጸዋል።
‎የቅድመ አንደኛና የአንደኛ ደረጃ ትምህርት መጽሐፍትን አንድ ለአንድ ለማድረስ ከ 23.9 ሚሊዮን በላይ መጽሐፍት ታትመው እየተሰራጩና እየተጓጓዙ እንደሚገኙም ጠቁመዋል።
‎የሥርዓተ ትምህርት ማበልጸጊያ ተጠባባቂ መሪ ሥራ አስፈጻሚ ወ/ሮ ዛፉ አብርሃ በበኩላቸው በአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት ትግበራ ሂደት ለስርጭት የተዘጋጁት የ2ኛ ደረጃ የብሬል መማሪያ ማስተማሪያ መጽሐፍት በስድስት (6) የትምህርት ዓይነቶች የተዘጋጁ መሆናቸውን ተናግረዋል።
‎የብሬል መጽሀፍቱ ለሁሉም ክልል አይነ ስውራን ተማሪዎች መታተማቸውን የገለጹት ወ/ሮ ዛፉ በአሁኑ ወቅት ታትመው የተጠናቀቁት የብሬል መጽሐፍት ከማዕከል ወደ ክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች ከሰኞ ጀምሮ እንደሚጓጓዙ ጠቁመዋል።
Recent News
Follow Us