News Detail

National News
Oct 15, 2025 20 views

በጎልማሶችና መደበኛ ያልሆነ ትምህርትና ሥልጠና ረቂቅ ደንብ ላይ የምክክር መድረክ ተካሄደ።

በምክክር መድረኩ ላይ የተገኙት የአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስቴር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ አየለች እሸቴ የጎልማሶችና መደበኛ ያልሆነ ትምህርት ፕሮግራም በተለያየ ጊዜ የተለያየ ስያሜ ተሰጥቶት ሲተገበር መቆየቱን አንስተዋል።
ይህ ፕሮግራም ለዜጎች አማራጭ የትምህረትና ሥልጠና እድል በማቅረብ ረገድ አስተዋፅኦው የጎላ ነው ያሉ ሲሆን ፕሮግራሙን በውጤታማነት ለመተግበር እንዲቻል የአጠቃላይ ትምህርት አዋጁን መነሻ በማድረግ የጎልማሶችና መደበኛ ያልሆነ ትምህርትና ስልጠና ረቂቅ ደንብ መዘጋጀቱን ጠቅሰዋል።
ከዚህ አንጻር በተዘጋጀው ረቂቅ ደንብ የሚመለከታችው ሴክተር መስሪያ ቤቶች ጋር ምክክር በማስፈለጉ እና ግብአት የሚሰበሰብበት ስለሆነ ይህ መድረክ መዘጋጀቱን ጠቅሰዋል ።
የጎልማሶችና መደበኛ ያልሆነ ትምህርት መሪ ሥራ አስፈፃሚ ዮሴፍ አበራ(ዶ/ር) በበኩላቸው ከዚህ በፊት ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ሴክተሮች ጋር የመግባቢያ ስምምነት በመፈራረም ፕሮግራሙ በቅንጅት ሲተገበር መቆየቱን አንስተዋል።
Recent News
Follow Us