News Detail

National News
Jan 28, 2025 223 views

የትምህርት ሚኒስቴር እና የጣሊያን ከፍተኛ ትምህርትና ምርምር ሚኒስቴር በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ ተፈራረሙ።

የስምምነቱን ሰነዱን የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ እና የጣልያን ከፍተኛ ትምህርት እና ምርምር ሚኒስትር አና ማሪያ ፈርመውታል።
የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በዚሁ ወቅት እንዳሉት በሁለቱ ሀገራት የተደረገው ስምምነት በትምህርቱ ዘርፍ የተጀመሩ ሥራዎችን ውጤታማ ለማድረግ የሚያግዝ መሆኑን ገልጸዋል።
በተለይም በትምህርት ዘርፍ በትብብር ለመስራት የሚያስችሉ ምቹ ሁኔታዎች እንዳሉ ገልጸው የሚደረገው ድጋፍ ፍትሃዊና ለታለመለት አላማ እንዲውል ማድረግ ይገባል ብለዋል።
አክለውም ዩኒቨርሲቲዎች ራስ ገዝ እንዲሆኑ እየተሰራ ያለውን ሥራ እና በትምህርቱ ዘርፍ ትብብር የሚሹ ጉዳዮችን ለሚኒስትሯ አብራርተውላቸዋል።
የጣሊያን የከፍተኛ ትምህርት እና ምርምር ሚኒስትር አና ማሪያ በበኩላቸው፥ ኢትዮጵያ የጣሊያን አጋር መሆኗን አንስተው ሁለቱ ሀገራት በትምህርቱ ዘርፍ በላቀ ትብብር እንደሚሰሩ ገልጸዋል።
የተፈረመው መግባቢያ ስምምነት በጣሊያን እና በኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መካከል ቀጥተኛ ትብብር እንዲኖር የሚያበረታታ ነው ተብሏል።
ከዚህም በተጨማሪም በጣልያን መንግስት እና UNOPS አጋርነት በኢትዮጵያ ለሚገነቡ ሁለት የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ግንባታ መግባቢያ ስምምነትም ሁለቱ ሚኒስትሮች በተገኙበት ተፈርሟል።
ስምምነቱን በኢትዮጵያ የጣሊያን አምባሳደር ኦግስቲኖ ፖሌሲ እና የአፍሪካ ቀንድ ባለብዙ ሃገራት የዩኖፕስ (UNOPS) ቢሮ ዳይሬክተርና የአፍሪካ ህብረት ተወካይ ወ/ሮ ወርቅነሽ መኮንን ፈርመውታል።
Recent News
Follow Us