News Detail

National News
Jan 17, 2025 17 views

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በኢትዮጵያ ከጀርመን አምባሳደር ጋር ተወያዩ።

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በኢትዮጵያ ከጀርመን አምባሳደር ጄንስ ሃንፊልድ ጋር ተወያይተዋል።
በውይይታቸው የትምህርት ሚኒስትሩ በትምህርት ሥርዓቱ ለዜጎች ጥራት ያለው ትምህርትን ተደራሽ በማድረግ ተወዳዳሪና ብቁ ትውልድ ለመፍጠር እየተተገበሩ ስላሉ የሪፎርም ሥራዎች እና ድጋፍ የሚሹ ጉዳዮችን ለአምባሳደሩ አብራርተዋል።
በዚህም የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ በትምህርት ዘርፉ እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን፣ በተፈጥሮና ሰው ሰራሽ አደጋዎች የተጎዱ የትምህርት ተቋማትን መልሶ ለመገንባት የሚደረገውን ጥረትና የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ራሳቸውን የሚያስተዳድሩ፣ ነጻ ሃሳብ የሚራመድባቸው፣ ትክክለኛ የማስተማሪያና የምርምር ተቋማት እንዲሆኑ ለማድረግ እየተወሰዱ ያሉ እርምጃዎችን እንዲደግፉም ጠይቀዋል።
በኢትዮጵያ የጀርመን አምባሳደር ጄንስ ሃንፊልድ በበኩላቸው ኢትዮጵያና ጀርመን ለረጅም ጊዜ የቆየ መልካም ግንኙነት እንደነበራቸው ገልጽው ይህንን አጠናክረው መቀጠል እንደሚፈልጉም ተናግረዋል።
በተለይም በክቡር ሚኒስትሩ የቀረቡትን በኢትዮጵያ የጀርመን ትምህርት ቤት ብቁና ተወዳዳሪ የሆኑ ተማሪዎች የነጻ የትምህርት እድል የሚያገኙበትን፣ በሰው ሰራሽና ተፈጥሮ አደጋ የወደሙ ትምህርት ቤቶችን መልሶ በመገንባትና በትምህርት ዘርፉ የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ እየተተገበሩ ያሉ የሪፎርም ስራዎችን በመደግፍ ረገድ የቅድሚያ ትኩረት ሰጥተው እንደሚሰሩም አብራርተዋል።
Recent News
Follow Us