News Detail
Aug 31, 2024
1.3K views
በትምህርትን ስራ ላይ ያሉ አመራሮች የትምህርትን ሥራ ከፖለቲካ በመለየት በትምህርት ስራው ላይ ብቻ ማተኮር እንዳለባቸው የትምህርት ሚኒስትሩ ክቡር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ አስገነዘቡ።
የሚኒስትሩ በ33ኛው አገር አቀፍ የትምህርት ጉባዔ ላይ እንደገለጹት በትምህርት ስራ የሚፈለገው ውጤት እንዲመጣ በትምህርትን ስራ ላይ ያሉ አመራሮች ትምህርትና ፖለቲካን መቀላቀል የለባቸውም ብለዋል።
የትምህርት አመራሮች ዋነኛ ስራ የትምህርትና የፖለቲካ ስራን ሳይቀላቅሉ በቅንነት መስራትና በሀቀኝነት ማገልገል ሊሆን ይገባል ሲሉ አሳስበዋ።
ትምህርትን በጥራትና በፍትሃዊነት ለዜጎች ለማቅረብ ለተጀመረው ሥራ ስኬትም ሁሉም የትምህርት ስራ ባለድርሻዎች ጠንክሮ መሥራት እንደሚጠበቅባቸውም ጠቁመዋል።
የአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ አየለች እሸቴ በበኩላቸው የትምህርት ጥራት ፣ ፍትሀዊነትና ተገቢነቱን ለማረጋገጥ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። ለዚህ ስኬታማነትየመምህራንን አቅም ማሳደግ አንዱ ተግባር በመሆኑ በዚህ ዙሪያ ስራዎች እየተሰሩ ነው ብለዋል።
ክብርት ሚኒስትር ዴኤታዋ አክለውም የመምህራንን የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ከክልሎች ጋር በመነጋገር ለመፍታት እየተሞከረ መሆኑን ጠቁመው ይሄው ስራም ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።
የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ደኤታ አቶ ኮራ ጡሹኔ በበኩላቸው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ስራዎቻቸውን በቁልፍ የአፈጻጸም አመላካቾች (KPI) በመለካት ለተሻለ ስራ መትጋት እንዳለባቸው አስገንዝበዋል፡።
በጉባኤው ላይ የክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊዎች ፣ የዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንቶች፣ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ፣ የመያ ማህበራት ፣ አጋሮች እና ሌሎችም እየተሳተፉ ይገኛሉ።
Recent News
በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የምግብ ሜኑ ተመሳሳይ እንዲሆን ተወሰነ።
Dec 09, 2024
የእንግሊዝኛ ቋንቋ ክህሎትን ለማሳደግ በትኩረት መስራት እንደሚገባ ተጠቆመ።
Dec 07, 2024