News Detail
Jan 11, 2024
767 views
የኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴር ከደቡብ ከኮሪያ ጋር በትምህርት ኢንፎርሜሽን ልውውጥና ትብብር ላይ የስምምነት ሰነድ ተፈራረመ ፡፡
የኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴር ከደቡብ ኮሪያ ጊዮንግሳንግቡክ-ዶ (Geongsangbuk-do) ትምህርት ቢሮ ጋር በትምህርት ኢንፎርሜሽን ልውውጥና ትብብር ዙሪያ በጋራ ለመስራት የሚያስችል የትብብር መግባቢያ ሰነድ ስምምነት ተፈራርሟል፡፡
የትብብር ስምምነቱ በሁለቱ ሃገራት መካከል ከ20016-2017 ዓ.ም የሚደረገውን የትምህርት ኢንፎርሜሽን ልውውጥና ትብብርን የተመለከተ ነው።
ስምምነቱ በሀገራቱ መካከል ያለውን የወዳጅነትና ድጋፍ ከማጠናከሩ ባሻገር በዲጂታል የትምህርት ስትራቴጂና የማስፈጸሚያ ዕቅድ አተገባበር እንዲዳብር ለማበረታታት ያስችላል ተብሏል፡፡
በትብብር ስምምነት ሰነዱ ላይ የአይሲቲ መሳሪያዎችን ማቅረብና ለተመረጡ መምህራን ከትምህርታዊ መረጃ አሰጣጥ ጋር የተያያዘ ስልጠና መስጠት የኮሪያ መንግስትን የሚመለከቱ መሆኑና የስልጠና ተሳታፊዎችን መምረጥን በተመለከተ የትምህርት ሚኒስቴርን የሚመለከቱ መሆናቸውን ተካተውበታል፡፡
የኢፌዲሪ ትምህርት ሚኒስቴር ሚንስትር ዴኤታ ወ/ሮ አየለች እሸቴ እና የጊዮንግሳንግቡክ-ዶ ቢሮ የትምህርት ዘርፍ አስተዳዳሪ ሊም ጆንግ-ሲክ በእለቱ ተገኝተው ስምምነቱን ፈርመዋል፡፡
Recent News
በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የምግብ ሜኑ ተመሳሳይ እንዲሆን ተወሰነ።
Dec 09, 2024
የእንግሊዝኛ ቋንቋ ክህሎትን ለማሳደግ በትኩረት መስራት እንደሚገባ ተጠቆመ።
Dec 07, 2024