News Detail

National News
Jul 06, 2023 4.7K views

በ6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 2ኛ ዓመት የስራ ዘመን 28ኛ መደበኛ ጉባዔ የትምህርት ዘርፍን በሚመለከት የተጠየቁ ጥያቄዎችና አስተያየቶች

1) ከ1ኛ እስከ 8ኛ ክፍል አዲሱ ስርዓተ ትምህርት ሲተገበር የተሟላ የመማሪያ መጽሀፍ አለመኖር፣ የትምህርት ግብዓት አለመሟላት፣ የቤተ ሙከራ የኬሚካል እጥረት፣ የቤተ ሙከራ መምህራን አለመኖር ችግሮች ናቸው። በ2016 ትምህርት ዘመን ችግሩ እንዳይቀጥል ምን ታስቧል?

2) በጦርነትና በልዩ ልዩ ግጭቶች የተጎዱ አካባቢዎችና ትምህርት ቤቶች መልሶ ለመገንባት ና  ትምህርት ተደራሽ ለማድረግ ምን እየተሰራ ነው፣
3) ዩኒቨርሲቲዎችን ራስ ገዝ የሚያደረግ አዋጅ ጸድቆ ተግባራዊ እየተደረገ ነው። ነገር ግን መክፈል የማይችሉ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ዜጎች የመማር እድል ሊያሳጣ ይችላልና ምን ታስቧል?

4) ዩኒቨርሲቲዎች ራስ ገዝ ሲሆኑ ከመንግስት የሚመደበው በጀት ይቋረጣል የሚል ሰጋት አላቸው፤ ይህ  እንዴት ይታያል?

5) ከሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃ ጋር በተያያዘ የሀሰተኛ የትምህርት አሰጣጡን ጨምሮ ቁጥጥር ላይ ችግሮች እንዳሉ ይነሳል፣ ችግሩን ለመፍታት ምን ታስቧል? 

6) የዩኒቨርሲቲ የማስተማሪያ ሆስፒታሎች ትምህርት ሚኒስቴር የሚያስተዳድራቸው በመሆኑ በጤና ሚኒስቴር የሚደረግላቸው ድጋፎች እጅግ አነስተኛ ነው፡፡ በሌላ በኩል በዩኒቨርሲቲዎቸ ያሉ ሆስፒታሎች የሰው ሀይልና ህክምና ማሽነሪዎች አቅም እጅግ ከፍተኛ ቢሆንም ከበጀትና ቅንጅታዊ አሰራር ጋር በተያያዘ በሙሉ አቅማቸው ማህበረሰቡን እያገለገሉ አይደለም ከዚህ አኳያ ቀጣይ የመንግስት ስራ ምን መሆን ይኖርበታል ማብራሪያ ቢሰጥ 
  ......

የክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩን ምላሽ በቀጣይ የምናቀርብ ይሆናል።

Recent News
Follow Us