News Detail

National News
Mar 10, 2023 2.7K views

በ2014 ዓ.ም 12ኛ ክፍል የላቀ ዉጤት ላመጡ ስለተሰጠዉ የዉጪ ሀገር የትምህርት እድል /Scholarship / አንዳንድ ነጥቦች፤-

በ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና ከተፈተኑ ተማሪዎች መካከል 3.3 በመቶ ተማሪዎች ብቻ ወደዩኒቨርስቲ የሚያስገባቸዉን 50/በመቶና በላይ ዉጤት ያስመዘገቡ ሲሆን ከነዚህ መካከል 263 የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች 600/700 እንዲሁም 10 የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች 500/600 በማምጣት የሀገሪ
እነዚህ 273 ተማሪዎች የካቲት 21/2015 ዓም በሀገር አቀፍ ደረጃ የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዓብይ አህመድ፣ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋና የአጠቃላይ ትምህርት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ፋንታ ማንደፍሮ እጅ የእዉቅናና ሽልማት ተቀብለዋል፡፡
በዚሁ እለት በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ ለእነዚህ ተማሪዎች በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ የትምህርት እድል/ Scholarship / እንደተገኘ ተገልጸል፡፡
በ2014 ዓም. የተጀመረዉ የፈተና ስርዓት ለዉጥ እንዲጠናከርና መንግስት ለትምህርት ዘርፉ የሰጠዉን ልዩ ትኩረት ለማሳየት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባደረጉት ጥረት ከወዳጅ አገራት የተገኘዉ ይህ የትምህርት እድል ተማሪዎች ከመስከረም/2016 ዓም ጀምሮ እንዲማሩ ተመቻችቷል፡፡
ወደዉጪ እስኪሄዱ ድረስ ያሉትን ግዜያት የእንግሊዝኛ ቋንቋ ማሻሻያ ትምህርት በመማርና ሌሎች ለወደፊታቸዉ የሚያግዙ ቅድመ-ዝግጅቶችን እያደረጉ እንድቆዩ የሚሰራ ይሆናል፡፡
እዚህ ላይ መታወቅ ያለበት አንድ ጉዳይ እነዚህ ተማሪዎች የተፈጠረላቸዉ እድል በቀጣይ እየተፈጠረ ላለዉ በዉድድር ላይ የተመሰረተ ዓለም እኛንም በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ የሚያደርጉ ምሩቃንንና ሳይንትስቶችን ፣ ቴክኖሎጂስቶችን፣ መሪዎችን የመፍጠሪያ ልዩ እድል ነው፡፡
በተጨማሪም ተማሪዎቻችን በሄዱበት የሀገር ስምና ገጽታ ናቸዉ ፡፡ በአቅማቸዉ ተወዳድረዉ በዓለም ደረጃ ስመጥር በሆኑ ዩኒቨርስቲዎች አሸንፈዉ ጥሩ ሆነዉ ተመርቀዉ በተሻለ ዉጤት ሲመጡ ኢትዮጵያ ዉስጥ ትምህርት ምን እንደሚመስል ሌላዉም ዓለም ይገነዘባል፡፡ ወደሀገራቸዉ ተመልሰዉ ሲያገለግሉም በፍጥነት ከድህነት ለመዉጣትና ወደብልጽግና ለመሄድ ለምናደርገዉ ስራ አጋዥ ይሆናል የሚል ፅኑ እምነት አለ፡፡
የተፈጠረዉ የትምህርት ዕድል በጣም ጥሩ እድል ነዉ፡፡ ነገር ግን ዕድሉ ለተፈጠረላቸዉ ተማሪዎች እንደግዴታ የሚወሰድ አይደለም፡፡ በጣም ትልቅ እድል፣ ከፍተኛ ጥረት ተደርጎበት በክቡር በጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ የተገኘ እድል ነዉ፡፡ በመሆኑም የአንድም ተማሪ እድል ሳይባክን መጠቀም ለሀገር ይጠቅማል፡፡ ይህንን በማድረግ ሂደት ዉስጥ ደግሞ ሁሉም የበኩሉን እንዲወጣ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡
ይሁን እንጅ ተማሪዎች መማር የምፈልገዉ በሀገር ዉስጥ ባሉ ዩኒቨርስቲዎች ነዉ ብለዉ ካሰቡ የሚገደዱበት ሁኔታ የለም፡፡
እነዚህ ተማሪዎች በተባበሩት ኤሜሬትስ በየትኞቹ ዩኒቨርስቲዎች ሊማሩ ይችላሉ?
በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ በአለም አቀፍ ደረጃ ስመጥር የሆኑ ብዙ ዩኒቨርስቲዎች ያሉ ሲሆን ስድስት ዩኒቨርስቲዎች QS World University Rankings® 2021 (https://www.topuniversities.com/.../world-university.../2021), የተካተቱ ሲሆን ስምንት ዩኒቨርስቲዎች ደግሞ በ 2023 QS Arab Region University Rankings (https://www.topuniversities.com/ arab-region-rankings) . ተካተዋል፡፡
በአረብ ኤምሬትስ ካሉ ዩኒቭርስቲዎች ትልቁ የተባበሩት አረብ ኤምሬተስ ከፍተኛ የቴክኖሎጂ ኮሌጅ ሲሆን በሀገሪቱ በአጠቃላይ 17 ካምፓሶች አሉት።
የተባበሩት አርብ ኤምሬትስ ዩኒቨርስቲ
-----------------------
የተባበሩት አርብ ኤምሬትስ ዩኒቨርስቲ በአለም አቀፍ ደረጃ 284ኛ ላይ ሲገኝ በአረብ ወሰጥ ካሉ ዩኒቨርስቲዎች ዉሰጥ ደግሞ አምሰተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። መቀመጫውንም አል አይን በተባለችው የአቡ ዳቢ ከተማ ሲሆን ካሉት ዩኒቨርስቲዎችም በእድሜ ትንሹ ነው።
አሜሪካን ዩኒቨርስቲ ኦፍ ሻርጃ
------------------------
አሜሪካን ዩኒቨርስቲ ኦፍ ሻርጃ በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ዉስጥ ካሉ ዩኒቨርስቲዎች በሰባተኛነት የተቀመጠ ሲሆን የሚሰጣቸው የትምህርት አይነቶችም በአሜሪካ የከፍተኛ ትምህርት ሞዴል መሰረት ነው። በአለም አቀፍ ተማሪዎችም ተመራጭ የሆነ ዩኒቨርስቲ ነው።
ካሊፋ ዩኒቨርስቲ
--------------------
ካሊፋ ዩኒቨርስቲ በአለም አቀፍ ደረጃ 211ኛ ላይ ሲገኝ በ2021 በተሰጠው የዩኒቨርስቲዎች ደረጃ ደግሞ በአረብ ዉሰጥ ካሉ ዩኒቨርስቲዎች ውሰጥ በ ዘጠነኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል። ካሊፋ ዩኒቨርስቲ ለትርፍ ያልተቋቋመ ትኩረቱን ሳይንስ ላይ አደረጎ በ 2007 የተመሰረተ ዩኒቨርሰቲ ነው። ዩኒቨርሰቲው በአሜሪካ የከፍተኛ ትምህርት ሞዴል የተቃኘም ጭምር ነው። ካሊፋ ዩኒቨርሰቲ በውሰጡ ሶሰት ኮሌጆች፣ ሶሰት የምርምር ኢኒስቲቲዩቶች፣ 18 የምርምር ማእከላት እና 36 ዲፓርትመንቶችን በተለያዩ የትምህርት መሰኮች ይዟል።
ዪኒቨርስቲ ኦፍ ሻርጃ
-------------------------
ዪኒቨርሰቲ ኦፍ ሻርጃ በ 1997 የተቋቋመ ሲሆን በመካከለኛው እሩቅ ምሰራቅ እና በአለም አቀፍ ደረጃ ቀዳሚ የትምህርት ተቋም ለመሆን አልሞ እየሰራ ያለ ዩኒቨርሰቲ ነው።
ዛይድ ዩኒቨርስቲ
በ1998 የተመሰረተዉ ዛይድ ዩኒቨርስቲ በQS World University Rankings® 2019 (https://www.top http://universities.com/.../world-university-rankings/2021). 701-750 መካከል የነበረ ነዉ፡፡
Recent News
Follow Us