News Detail

National News
Mar 01, 2023 2.4K views

"የአድዋ ድል በዓል ለኢትዮጵያውያን ብቻ ሣይሆን ለመላው ጥቁር ህዝቦች ኩራት የሆነ የድል በዓል ነው" ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ፣ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ትምህርት ሚንስትር

የካቲት 22/2015 (የትምህርት ሚኒስቴር) የትምህርት ሚኒስቴር አመራሮችና ሠራተኞችና 127ኛውን የአድዋ ድል በዓል በተለያዩ ዝግጅቶች አክብረዋል።
"የአድዋ ድል በዓል ለአገራዊ አንድነት፣ጀግንነት እና ጽናት መልህቅ" በሚል መሪ ቃል በተከበረው የድል በዓል ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የትምህርት ሚንስትሩ ፕ/ር ብርሀኑ ነጋ የአድዋ ድል ለኢትዮጵያውያን ብቻ ሣይሆን ለመላው ጥቁር ህዝቦች ኩራት የሆነ የድል በዓል ነው ብለዋል።
ሚንስትሩ በመልዕክታቸው አያይዘው እንደተናገሩት የአድዋ ድል በአል የሁሉም ብሄር ብሄረሠቦችና ህዝቦች የድል በዓል በመሆኑ ልዩነትና የጠብ መነሻ አድርጎ ለማሳየት የሚሞክሩ ሀይሎችን እምቢ ማለት ይገባል ብለዋል።
የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታው ዶ/ር ሣሙኤል ክፍሌ በበኩላቸው የአድዋ ድል በጋራ ቆሞ፣በቁርጠኝነት ሠርቶ ፣በጽናት ታግሎ በመቆም የበለፀገች ሀገር በመገንባት እንዴት ለትውልድ ማስረከብ እንደሚቻል ታላቅ ትምህርት የምንቀስምበት የድል በአል ነው ብለዋል።
የአጠቃላይ ትምህርት ዘርፍ ሚንስትር ድኤታ ዶ/ር ፈንታ ማንደፍሮ በማጠቃለያ ንግግራቸው በዚህ ዘመን ከላይ እስከ ታች ያለን አመራሮች ከአድዋው ድል የመሪነት ጥበብ እና አንድነት ሀይል መሆኑን ተገንዝበን በተሠማራበት ሙያና መስክ ውጤታማነትን ማረጋገጥ ይገባናል ብለዋል።
የአድዋ ድል ቱርፋቶችን አስመልክቶ በትምህርት ሚኒስቴር የማህበራዊ ት/ቶች ስርዓተ ትምህርት ዴስክ ሀላፊ አቶ ኡመር ኢማም በቀረበው የመነሻ ሀሣብ ጽሁፍ ላይ ተሣታፊዎች ሠፊ ውይይት አርገውበታል።
በፕሮግራሙ መነባነብና አጭር ትወና በወ/ሮ አታላ ውቤ ቀርቧል።
Recent News
Follow Us