News Detail

National News
Mar 01, 2023 2.3K views

በሚቀጥሉት ሰባት ዓመታት በአገሪቱ ሁሉንም የመጀመሪያ ደረጃ ተማሪዎች የምገባ ተጠቃሚ ለማድረግ እየተሰራ ነው:- የትምህርት ሚኒስቴር።

የካቲት 22/2015 ዓም (የትምህርት ሚኒስቴር) የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ በ8ኛው የአፍሪካ የትምህርት ቤት ምገባ ቀን በዓል ላይ እንዳሉት እ.አ.አ.በ2030 በሁሉም የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የምገባ መርሀ ግብር በማስፋት ቢያንስ አንዴ የምገባ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ይደረጋል።
የትምህርት ቤት ምገባ መርሀ ግብር ለትምህርት ጥራት ከሚያበረክተው አስተዋጽኦ ባሻገር የምግብ ፍጆታ ግዢ ስርዓት እና ሌሎችም የአቅርቦት እሴቶችን ለማሳደግ እንደሚያስችልም ፕሮፌሰር ብርሀኑ ተናግረዋል።
ለ8ኛ ጊዜ የሚከበረው የአፍሪካ የትምህርት ምገባ ቀን መልካም ተሞክሮዎችን ለማጋራት እድል የሚፈጥር መሆንንም ሚኒስትሩ አስረድተዋል።
የአዲስአበባ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በበኩላቸው በከተማው እየተካሄደ ያለው የትምህርት ቤት ምገባ መርሀ ግብር ዓለም አቀፍ ዕውቅና የተቸረውና በትምህርት ቤቶች በተማሪዎች ላይ ሲከሰት የነበረውን የአጭር ጊዜ ረሀብ መቅረፍ ማስቻሉን ገልጸዋል።
መርሀ ግብሩ የወላጆችንም የወጪ ጫና ከመቀነስ በተጨማሪ የተማሪዎችንም የትምህርት ተሳትፎና ውጤታማነት ማጎልበቱን ጠቁመዋል።
በዓለም ምግብ ፕሮግራም ትምህርትን መሠረት ያደረጉ ፕሮግራሞች ዳይሬክተር ሚስ ካርመን በርባኖ ባቀረቡት ሪፖርት የትምህርቶ ቤት ምገባ ተጠቃሚ ህጻናት ቁጥር በዓለም አቀፍ ደረጃ እያደገ ቢሆንም ዝቅተኛ ገቢ ባላቸው የአፍሪካ አገራት የተጠቃሚ ህጻናት ቁጥር በ16 %(በመቶ) መቀነሱን ተናግረዋል።
'በዓሉ የተከበረው 'የአገር ውስጥ የምግብ ፍጆታ ግዢ ስርዓትና ቀጣናዊ የአቅርቦት እሴቶች በማሳደግ ቀጣይነት ያለው አገር በቀል የትምህርት ቤት ምገባን በማረጋጥ ትምህርትን ማሻሻል'በሚልመሪ ቃል ነው።
Recent News
Follow Us